የህዳሴን ግድብ ለመጠበቅ ዲቪዥኝ በሚል ስያሜ በግድቡ የተሰማሩ የፌደራል ፖሊስ አብላት በሚያዝያ
27,2005 ዓ/ም በዲቪዥኑ ሁለት ክላስተሮች አስተባባሪ በሆነው ኮማንደር ሰለሙን አብርሃም ሲመራ በነበረ ስብሰባ በርካታ ጥያቄዎች
ተነስተዋል።
በሰራዊቱ ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል የደመውዝ ጭማሪ ፣ የበርሃ አበል ፣ የአልባሳት ችግር ፣ የምግብ ጥራትና
አቅርቦት መጓደል ፣ የስራ መልቀቅያን ፣ የእረፍት ፈቃድና ሌሎች የሚገኙባቸው ሲሆኑ በሚመለክተው አካል አጥጋቢ ምላሽ ሳይሰጣቸው
ቀርቷል ።
በተሰጠው ምላሽ የተከፉ የሰራዊቱ አባላት ለጥያቅያችን የምትሰጡት ምላሽ እንዲህ ከሆነ ባትመጡ ይሻል ነበር
በማለት በየግላቸው ለመውሰድ ያሰቡትን እርምጃ በግልጽ በማቅረብ ፣ ስራውን እየጣለ የሚጠፋ አባል ቁጥር እንደሚጨምርና በግልጽ በመድረኩ
መሮናል በዚህ ሁኔታ መቀጠል አንችልም በሚል የቀረበ ቁጣ የተቀላቀለበት ንግግር በአብዛኛው ተሰብሳቢ ስለተደገፈ ስብሰባውን ሲመራ
የነበረ ኮማንደር ሰለሙን ቁጣውን መቆጣጠር አቅቶት መድረኩን ረግጦ እንደሄደና ስብሰባውንም ያለ ምንም ፍሬ መበተኑን ለማወቅ ተችሏል።