በአማራ ክልል ፤ በአዊ ዞን ፤ አንካሻ ወረዳ በሟሟያ ምርጫ የተሳተፉና አቋማቸው በተቃዋሚነት የሚታወቁ
ሰዎችን የእጅ ጽሁፍን በመለየትና ከቃላቸው በማረጋገጥ ለምን ኢህአዴግን አልመረጣችሁም በሚል በስርዓቱ የጸጥታ ሃይሎች ጥብቅ ክትትል
እንደሚደረግባቸውና ማንኛውንም ጥቅማጥቅምም እንዳያገኙ እየተደረገ መሆኑን ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣፣
ለምን ተቃዋሚን መረጣችሁ በማለት ሰዎችን እያዋክውቡ ካሉ ባለስልጣናት መካከል አቶ ባይነሳኝ አለሙና አቶ
ቢተው ካሳሁን የምርጫ አስተባባሪዎች እንዲሁም አቶ ጌታየ ሁነኝ የወረዳው አስተዳዳሪ ይገኙበታል፣፣
የኢህአዴግ
ስርዓት ሆን ብሎ የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ሲል ለምን የተቃዋሚ ድርጅትን መረጣችሁ በሚል ምክንያት የዜጎችን ዴሞክራሲያዊ መብት
በመርገጥ እየፈጸመው ያለው ኢሰብአበዊ ተግባር ኢህአዴግ እራሱ ላጸደቀው ህገመንግስትንና የመድብለ ፓርቲ ስርዓትን ተገዥ ያለመሆኑን
የሚያሳይ ነው ሲሉ የአከባቢው ናሪዎች ይናገራሉ፣፣