Saturday, May 11, 2013

ኗሪነታቸው በአንካሻ ወረዳ የሆኑ የብሄረ አማራ ተወላጆች የኢህአዴግን መንግስት ትቃወማላችሁ በሚል ምክንያት እየታሰሩ መሆኑ ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።



በደረሰን ዘገባ መሰረት በአማራ ክልል ፣ አዊ ዞን ፣ በአንካሻ ወረዳ ፣ የአማራ ብሄር ተወላጆች የገዥው ፓርቲ ደጋፊዎች ባለመሆናቸው ብቻ ጸረ-ልማት ፣ የአሸባሪዎች ተባባሪዎች ናቸው በሚል ሰበብ በፖሊስ እየተያዙ እንዲታሰሩ እየተደረገ ይገኛል። ግለሰቦቹ የሚያሳስር ወንጀል ስለሌላቸው ያለ ፍርድ ቤት እውቅና እስር ቤት በመቀያየር እያሰቃያቸው መሆኑን ለማወቅ ተችለዋል።
ምንም ወንጀል ሳፈጽሙ በፖሊስ ተይዘው ከታሰሩት የአከባቢው ኗሪዎች መካከል
1-       አቶ አይኑ
2-       አቶ ጥሩንርህ
3-       አቶ አይናቸው
የሚባሉ ዜጎች የሚገኙባቸው ሲሆን የስርዓቱ ካድሬዎች የዜጎችን ሰብአዊ መብት በመጣስ በግለሰቦች ላይ የቂም በቀል እርምጃ በመውሰድ ላይ ናችው።
ስርዓቱን በመቃወማቸው ብቻ እንደ ወንጀለኛ ተቆጥረው የተለያየ ስም እየተሰጣቸው በፈጠራ ወንጀል በየእስር ቤቱ በማጎር የሚፈጸመውን ግፍ የተገነዘቡ ፖለቲከኞችና የህግ አዋቂዎች ሁኔታውን አጥብቀው ማውግዛቸውን የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል።