Monday, June 3, 2013

ጉንበት 20 ለኛ ለኢትዮጵያዊያን እንደ ጠበቅነው ሳትሆን በአንጻሩ ጭቆናን ይዛብን ነው የመጣችው ሲል የትህዴን ሊቀመንበር ታጋይ ሞላ አስገዶም በዚሁ ሳምንት ከኢሳት ጋር ባደረገው ቃለ መጠየቅ ለገጸ፣


የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ(ትህዴን) ሊቀ-መንበር ታጋይ ሞላ አስገዶም ከኢሳት ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ ጉንበት 20 ለኢትዮጵያዊያን ነጻነት ሳይሆን የጨለማ ዘመንን ነው ያመጣችባችው በማለት በጉንበት 20,1983 ዓ/ም ስልጣንን የተቆጣጠሩ የኢህአዴግ አመራሮች 17 ዓመታት ለውጥ ፍለጋ የታገልውን ህዝብ ጥያቄ መልስ ያገኙ ዘንድ በተግባር ተንቀሳቅሰው አያውቁም ፣ እርግጥ ነው ፥ በመጀመሪያ አከባቢ ለህዝብ የገቡለት ቃል ነበር ፣ እያንዳንዱ ሰው በቀን ሦስት ጊዜ ይበላል ፤ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ይሰፍናል ወዘተ የሚል ንግግርና የተወሰነ ጭላንጭል ካልሆነ ባለፉት 22 ዓመታት የስልጣን ዘመናቸው አጭር ጊዜ ባይሆንም ለህዝብ የሚጠቅም ስራ ሳይስራበት ነው የባከነው ፣
ኢህአዴግ በተግባር የሚሰራ መንግስት ቢሆን ኖሮ በ 22 ዓመታት ይቅርና በ 5 ዓመታት ውስጥ በፖለቲካው ፤ በኢኮኖሚውና በማህበራዊው መስክ የተሻለ ለውጥ ማምጣት በቻለ ነበር ፣ ቢሆንም ግን የህዝቡን ኑሮ በተመለከተ ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ከመጣበት እለት ጀምሮ የታየ ለውጥ የለም፣ ነገሮች እየባሱ ነው የሄዱት በቀን ሦስት ጊዜ መመገብን ይቅርና በቀን አንዴ መመገብም ቢሆን ወደ እማይቻልበት ደረጃ ተደርሳል፣ በዚህ ላይ የዋጋ ንረት ተጨምሮበት ኑሮውን መምራት የተቸገረው አምራቹ ሃይል ወጣቱ ይሁን የመንገስት ሰራተኛው አገሩን እየተወ ዋስትና በሌለው በስሃራ በርሃ ባህርን አቋርጦ ለመሰደድ በሚያደርገው አደገኛ ጉዙ እራሱን ለስቃይና መከራ ብሎም ለሞት የሚዳርግበት አጋጣሚ ነው በተጨባጭ እየታየ ያለው ሲል ገልጻል፣
ታጋይ ሞላ በማያያዝም በስልጣን ላይ ያለው የኢህአዴግ ምንግስት በሰላማዊ መንገድ ተወዳድሮ ስልጣን መያዝ እንደሚቻል የሚነዛው ወሬ ለፕሮፖጋንዳ ፍጆታ ካልሆነ በተግባር ሊገለጽ የማይችል ቅጥፈት መሆኑን ድርጅታችን ትህዴን ከመጀመሪያውኑ ጀምሮ ስለደረሰበት  ህዝቡን በሃይል ጨፍልቆ በመግዛት ላይ ላለው አምባገነናዊ ስርዓት ሌላ አማራጭ እስከ ሌለ ድረስ የግድ በሃይል ለማስወገድ የተወሰደው አማራጭ ትክክል ሆኖ እነሆ ድርጅታችን በአሁኑ ጊዜ በሁሉም ረገድ አምባገነኑን ስርዓቱ በሚገባው ቋንቋ ለማነጋገር በሚያስችለው አስተማማኝ ደረጃ ላይ ይገኛል፣
በመቀጠልም ታጋይ ሞላ ድርጅታችን ትህዴን የትግራይ ህዝብ በጉንበት 20 ተጠቃሚ ነው የሚል የተዛባ አመለካከት የነበራቸው አንዳንድ ግለሰቦችን በማረም አንዲትና የበለጸገች ዜጎቻ በእኩልነት ተጠቃሚ የሚሆኑባት ኢትዮጵያን እውን እንድትሆን በፕሮግራማችን በግልጽ አስቀምጠናል ብቻ ሳይሆን በተግባርም በማይናወጥ ዓላም ነፍጥ አንስተን በመታገል ላይ መሆናችንን ማንም ሰው ሊያውቅ ይገባል ሲል አስገንዝቧል፣
የትህዴን በብሄር መደራጀት ስልታዊ ሆኖ የሚያካሂደው የትጥቅ ትግል ግን ለአንዲት ኢትዮጵያ እስከሆነ ድረስ በውስጡ ከሁሉም የሃገራችን ብሄር ብሄረ ሰቦች የመጡ ታጋዮችን ያቀፈ ሰፊ ራእይ ያለው ድርጅት ነው ሲል ገልጻል፣
በመጨረሻም ታጋይ ሞላ በትጥቅ ትግል በቂ የሰው ሃይልና ትጥቅ ብቻ መኖር ለድል እንደማያበቃ ጠቅሶ የሰው ሃይልና ትጥቅ እንዳለ ሆነ ከዛ በላይ ለመራመድ ግን ከጠላትህ በተሻለ ወታደራዊ አቅምና የበላይነት መጨበጥ አስፈላጊ ነው ፣ ይህንንም ቢሆን አረጋግጠነዋል፣ በመሆኑም ትህዴን በአሁኑ ጊዜ በስልጣን የሚገኘውን አምባገነናዊ የኢህአዴግ ስርዓትን ለማስወገድ የሚያስፈልገውን አቅም ገምብታል፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ይህንን ተረድቶ ከሱ የሚመጠበቅበትን ሁሉ ማበርከት ይጠበቅበታል ሲል አሳስባል፣