Monday, June 3, 2013

በአማራ ክልል ፤ በአዊ ዞን ፤ ዳንግላ ወረዳ ጉንበት ሃያን ምክንያት በማድረግ በመንግስት በተጠራው የድጋፍ ሰላማዊ ሰልፍ ህዝቡ አለመሳተፉን ከአከባቢው የደረሰንዘገባ ያመለክታል፣



ህዝቡ በሰላማዊ ሰልፉ ባለመገኘቱ ቅር የተሰኙት የስርዓቱ ባለስልጣናት ጉንበት ሃያን እንዴት ነው እያከበርነው ያለ? በዓሉን እንዴት ነው የምናየው ? ህዝቡ ለምን ከመንግስት ጎን አልተሰለፈም? የሚሉና የመሳሰሉ ጥያቄዎችን በማንሳት በአከባቢው ኗሪ ህዝብ ላይ ጫና በማደረግ ሊያስፈራሩት ሞክረዋል ይሁን እንጂ ህዝቡ እንደተቀበልው ታውቋል፣
በተለይ ኗሪነታቸው በአከባቢው በሆኑ ነባር ታጋዮች ከፍተኛ ተቃውሞ መቀስቀሱንና የታገልንለት ዓላማ አልተረጋገጠም ፤ መልካም አስተዳደር አልሰፈነም ስለዚህ ጉንበት ህያን ስናስብ በስርዓቱ የተፈጸመውን ክህደት ነው የምናስበው በማለት በስርዓቱ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ መግለጻቸውን የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል፣