Monday, June 3, 2013

በወልቃይት ወረዳ ፤ በማይ ገባ አከባቢ እየተገነባ ያለው የስኳር ፋብሪካ ንብረት በፋብሪካው ስራ አስከያጅ መዘረፉን ቷውቋል፣



በትግራይ ክልል ፤ በማይ ገባ አከባቢ እየተገነባ ባለው የስኳር ፋብሪካ ፕሮጀክት እንዲመሩ በስራ አስከያጅነት ተመድበው በመስራት ላያ ያሉት አቶ ጸጋይ ፍትዊ ለፋብሪካው ግምባታ አገልግሎት እንዲውል የተገዛውን ንብረት ለግል ጥቅማቸው ለማዋል በማሰብ ጉንበት 8,2005 ዓ/ም ፕሮጀችቱ ካለበት አከባቢ የተወሰነ ንብረት በመኪና በመጫን ሲወጡ የአከባቢው ህዝብና የፕሮጀችቱ ሰራተኞች  ከተዘረፈው ንብረት ጋር ስራ አስከያጁን እጅ ከፈንጅ በመያዝ ማይ ገባ ወደሚገኘው ፖሊስ ጣብያ ማስረከባቸው ታውቋል፣
ይሁን እንጂ ስራ አስከያጁ ስልጣንን አለአግባብ በመጠቀምና ከአከባቢው የፖሊስ አዛዥ ጋር በመመሳጠር ጠቀም ያለ ጉቦ በመክፈል ለአንድ ቀንም ቢሆን በማረፊያ ቤት ሳይቆዩና ጉዳዩ ሳይጣራ በነጻ እንዲለቀቁ ተደርጓል፣ የአከባቢው ኗሪም በሁኔታው እጅግ መቆጣቱን የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል፣