Monday, June 3, 2013

በጎንደር ከተማ የዘጠኝ ዓመቷን ህጻን አስገድዶ ለደፈረው ግለሰብ በከተማዋ ፍርድ ቤት የተሰጠው ብይን ፍትሃዊ አይደለም ሲሉ የአከባቢው ኗሪዎች ተቃወሙ፣



ሰላማዊት ካሳ የተባለች የዘጠኝ ዓመት ህጻንን መጋቢት 7/05 ዓ/ም አስገድዶ ከደፈረ ብሁዋላ እራሱን ሰውሮ የቆየው መሓመድ ኑሪ የተባለ ግለሰብ ከብዙ ፍለጋ ብሁዋላ በህዝቡ ትብብር በቅርቡ በቁጥጥር ስር ውሎ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ቀርቦ ግለሰቡ በስድስት ዓመት እስራት እንዲቀጣ ተፈርዶቦታል፣
የተሰጠው ብይም የሃገሪቱን የወንጀለኛ መቅጫ ህግን ያላገናዘበ ፤ በጉቦና ጥቅማ ጥቅምን መሰረት ያደረገ ፤ የሴቶችን መብት የጣሰና ወንጀሎኞችን የሚያበረታታ ሲሆን ፖሊስ ፤ አቃቢ ህግና ጉዳዩን የያዙት ዳኞች ጭምር ከተከሳሹ ጠቀም ያለ ገንዘብ በመቀበል ፍትህን ረግጠው በሰጡት ፍርደ ገምድል ውሳኔ ቅር የተሰኘው የከተማዋ ኗሪ ህዝብ ቁጣውን መግለጹን ለማወቅ ተችሏል፣