Monday, July 15, 2013

በአማራ ክልል በመተማ ወረዳ ሽህዲ ከተማ በፌደራል ፖሊስና በኢህአዴግ ስርዓት የመከላከያ ሰራዊት መካከል ሰኔ 28 እና ሃምሌ 2,2005 ዓ/ም የተኩስ ልውውጥ መደረጉን ቷውቋል።



በተደረገው የተኩስ ልውውጥ ከመከላከያ ሰራዊት ሃሰን ከድርና መስፍን ታፈሰ የተባሉ ሁለት ወታደሮች ወዲያውኑ የሞቱ ሲሆን፥ ከፌደራል ፖሊስ ደግሞ እሙት አዊ የተባለ አባል የሚገኝባቸው አራት የፖሊስ አባላት ተገድለዋል፣ የግጭቱ መነሻ በኮንትሮባንድ ስም ከነጋዴዎች የተነጠቀውን ንብረት ለግል ጥቅማቸው ለማዋል ባደረጉት እሽቅድድም የተፈጠረ ልዩነት መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
በሱዳን ድምበር የሚገኘው የመተማ ወረዳ በሁለቱ ሃገራት በሚደረገው የንግድ ልውውጥ መቆጣጠር የሚገባቸው የጉሩክ ሰራተኞች ቢሆኑም የኢህአዴግ ስርዓት ግን የፌደራል ፖሊስና የመከላከያ ሰራዊት አባላትን በተጨማሪ ሃይል ስለመደባቸው በቦታው የሚገኙ የሁለቱም ክፍሎች አዛዦች በአቋራጭ ሃፍት ለማካበት በሚያደርጉት መሯሯጥ አባሎቻቸው እርስ በእርሳቸው እስከ መገዳደል እንደሚደርሱ የሚታወቅ ነው።