Wednesday, July 10, 2013

በሽረ-እንዳስላሰ ከተማ በወርቅ ንግድ ስራ የተሰማሩ ዜጎች ፍትሃዊ ያልሆነ ግብር እንዲከፍሉ እየተገደዱ መሆኑን ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።



በደረሰን ዘገባ መሰረት በሽረ-እንዳስላሰ ከተማ የሚገኙ ነጋዴዎች ከገቢያቸው ጋር የማይመጣጠን ግብር እንዲከፍሉ እየተገደዱ ሲሆን አብዝኛዎቹ ነጋዴዎች ከአቅማችን በላይ ግብር እንድንከፍል ተወስኖብናል በማለት ዳግም እንዲታይላቸውና መፍትሄ እንዲሰጣቸው ለሚመለከተው አካል ጥያቄ አቅርበዋል ። ነገር ግን የተጠየቃችሁትን ክፈሉ እማትከፍሉ ከሆነ ንብረታችሁን በመውረስ ድርጅታችሁን እዲታሸግ እናደርጋላአን የሚል ምላሽ እንደሰጣቸው ቷውቋል።
ይህ በእንዲህ እያለ ከትግራይ ምስራቃዊና ማእከላዊ ዞን በዓዲ ጎሹና በዓዲ አሰር መካከል በሚገኝ ነጻ መሬት አርሰው እንዲጠቀሙ  የሔዱት ገበሬዎች በታሕታይ አድያቦ ፖሊስና አስተዳደር በመታገዳቸው ላልተፈለገ ድካምና ኪሳራ ተዳርገው በስርዓቱ ላይ ያላቸው ጥላቻ በመግለጽ ላይ ይገኛሉ።