Wednesday, July 10, 2013

መፍትሄ ባጣው የሸራሮ ከተማ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር ምክንያት የከተማዋ ኗሪዎች በተለያዩ የውሃ ወለድ በሽታዎች እየተሰቃዩ ነው።



የሸራሮ ከተማ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር ብዙ አመታት ያስቆጠረ ሲሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መጥቶ በአሁኑ ጊዜ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በመቆሙ የአከባቢው ህዝብ ንጽህናውን ያልጠበቀ የጉድጓድ ውሃ ለመጠቀም ተገዳል ። በዚህም ምክንያት በርካታ ህጻናት የሚገኙባቸው የከተማዋ ኗሪዎች በውሃ ወለድ በሽታ መጠቃታቸውን ቷውቋል።
በተመሳሳይ የሽረ-እንዳስላሰ ከተማ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር ስላልተፈታ በአሁኑ ጊዜ ከፍተኛ የመጠጥ ውሃ እጥረት በከተማዋ በመከሰቱ ኗሪው ጥራቱን ያልጠበቀ የጉድጓድ ውሃ ለአንድ ጀሪካን በ ሦስት ብር ሂሳብ ለመግዛት ተገዳል ። በተለይም አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች በውሃ እጦት የተነሳ ለኪሳራ መዳረጋቸውን ለማወቅ ተችሏል።
በከተማዋ በሚገኘው እስር ቤት የሚገኙ በሽዎች የሚቆጠሩ እስረኞችም በውሃ እጦት የተነሳ የግልም ሆነ አከባቢያዊ ንዝህና መጠበቅ ስላልቻሉ ለተባይና ለተለያዩ በሽታዎች ተጋልጠው በከባድ ችግር ላይ እንደሚገኙ የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል።