በከተማዋ በየቀኑ በርካታ ሰዎች በስርዓቱ የደህንነት አባላት እየታፈኑ የሚወሰዱ ሲሆን ፤ የተቃዋሚ ድርጅቶችን
ትደግፋላችሁ በሚል በዚሁ ሳምንት ታፍነው ከተወሰዱ የከተማዋ ኗሪዎች መካከል፣-
1-ሻለቃ ጌታቸው አላምረው የ 37ኛ ክ/ጦር አባል የነበረ
2-መምህር አወጠሀኝ ይደግ
3-ሙክታር ኢድሪስ የፖሊስ አባል የነበረ የሚገኙባቸው ሲሆን እነዚህ ዜግች በስርዓቱ የጸጥታ ሃይሎች አድራሻው
ወዳልታወቀ ቦታ ታፍነው መወሰዳቸውን የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል።
በአሁኑ ጊዜ ኗሪው ህዝብ ስርዓቱ ባሰማራቸው የጸጥታ አባላት ምክንያት የከተማዋ ኗሪ በሰላም እለታዊ ስራውን
ለመስራት አልቻሉም ። ለህልውናው ዋስትና አጥቶ በስጋት ውስጥ እንደሚኖር ለማወቅ ተችሏል።