በደረሰን መረጃ መሰረት በትግራይ ሰሜናዊ
ምእራብ ዞን በሸራሮ ከተማ የሚገኙ የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች በስርዓቱ አስተዳዳሪዎች የተለያዩ ተስፋ አስቆራጭ ሃሳቦች
በመሰንዘርና ወደፊት ዩኒቨርሲቲ ወስጥ ገብተው ቢጨርሱም እንኳን አሁን ካጋጠማቸው የስራ እድል የበለጠ እንደማያገኙ በመጥቀስና፤
ከተማ ውስጥ ከሚገኙ ተምረው ስራ ካጡ ወጣቶች መማር እንዳለባቸው በማደናገር፤ ሳይወዱ ወደ መከላከያ ሰራዊት እንዲገቡ ለማስቻል
የተቻላቸውን መሰሪ ተንኮሎች እየተጠቀሙ እንደሆነ ለማወቅ ተችለዋል፣
በወቅቱ እየተካሄደ በነበረው መጠነ
ሰፊ የቅስቀሳ ስብሰባ ውስጥ የተገኙ የተማሪዎቹ ወላጆች ተቸግረን ያስተማርናቸው ልጆቻችን በከንቱ ሂወታቸው እንዲከፍሉ መርቀን አንልክም!
የዚህ በፊቱ ይበቃናል! ሌላ ኣርእስት ካላችሁ ብታመጡ ይሻላቹኋል በማለት፤ ለቀረበው ጥሪ እንደተቃወሙት መረጃው ገልፀዋል፣
በሌላ በኩል በከተማው ውስጥ በተለይ
በአውቶብስ መናሃርያ አካባቢ በህጋዊ መንገድ መሬት ተሰጥቶዋቸው ደረጃው የጠበቀ ቤት ለሰሩ ወገኖች፤ በከተማው ማዛጋጃ ቤት የሰራችሁት
ቤት በመሃንዲስ ተቀባይነት ስላላገኘ አፍርሱት የሚል ትእዛዝ ተሰጥቶዋቸው ካፈረሱት በኃላ፤ የማዛጋጃ ቤት ሰራተኛ የሆነው አቶ አታክልቲ
የተባለ ግለሰብ ግን በቦታው ቤት ሰርቶ የንግድ ስራ እያካሄደበት እንደሆነ ለማወቅ ተችለዋል፣
ይህንን ለአንዱ ወገን ጠቅመህ ሌላኛውን
የመጉዳት መርህ የተከተለ የህወሃት ስርዓት አሰራር፤ ከግዜ ወደ ግዜ አይን ያወጣና በሁሉም የአገራችን ከተሞች እየተጠቀሙበት በመሆኑ
ህዝቡ ለዚሁ ብልሹና የተዛባ አካሄድ በተደጋጋሚ እየተቃወመው እንዳለ መረጃው አክሎ አስረድተዋል፣