Saturday, January 11, 2014

በታህታይ ኣድያቦ ወረዳ በህጋዊ መንገድ በማህበር ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ የቆዩ ወጣቶች በኣካባቢው መስተዳድር ስራቹህን ኣቓርጡ ስለ ተባሉ ችግር ላይ መውደቃቸው ተገለፀ፣



     በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ታህታይ ኣድያቦ ወረዳ ኣዲ ኣሰር ጣብያና ኣከባቢው የሚገኙ ዕጣን ማሕበር ኣዲ ኣሰር በሚል መጠርያ ስም የተደራጁ ወጣቶች። በወረዳዋ ኣስተዳደር ህጋዊ የስራ ፍቃድ በተሰጣቸው መሰረት ባሁኑ ኣመት ከከፈሉት 28 ሺ ብር በተጨማሪ በያመቱ ለመንግስት ግብር እየከፈሉ ቢቆዩም። ምክንያቱ ግልጽ ባልሆነ መንገድ። ካሁን ወድያ በኣከባቢው ዕጣን ሲለቅሙ ከተገኙ የኣካባቢው ኣስተዳደር እርምጃ እንደሚወስድላቸው ማስጠንቀቅያ ስለ ሰጣቸው ከስራዎቻቸው ተስተጓጉለው በችግር እንደወደቁ የደረሰን መረጃ ኣስታወቀ፣
    
     እነዚህ ከሁለት ኣመት በላይ በእጣን ለቀማ ስራ ላይ ተሰማርተው የቆዩ ወጣቶች ከልክ በላይ የሆነ ግብር ከከፈሉ በኋላ ለምን እንደተከለከሉ ለማወቅ የማህበርዋ ሊቀመንበርና ሌሎች ሰባት ኣባላት በመሆን ለታሕታይ ኣድያቦ ወረዳ ኣስተዳዳሪ ቢጠይቁም። ተገቢ መልስ የሚሰጣቸው ኣካል ባለማግኘታቸው ምሬታቸው በመግለጽ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችለዋል፣
    
    ይህ በንዲህ እንዳለ በሸራሮ ከተማ የኣላቂ ነገሮች ዋጋ ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ እንደሚገኝና። በተለይ ስኳርና ዘይት ከገበያ ጠቅልለው ስለ ጠፉ ከማከፋፍያ ጣብያ ኣንድ ሊትር ዘይትና ኣንድ ኪሎ ስኳር ብቻ ለመግዛት  የሆነ ሰው በነፃ ጉልበት እየተሰራ ባለው የእርከን ስራ ውስጥ እነደተሳተፈ የሚገልፅ ማረጋገጫ እንዲያመጣ እየተገደደ መሆኑንና። በእርከን ስራው ውስጥ ለመካፈል ኣቅም የሌላቸው የቤተሰብ ኣባሎችም  በከባድ የማህበራዊ ችግር ውስጥ ወድቀው እንደሚገኙ ምንጮቻችን ጨምረው ኣስታውቀዋል፣