Saturday, January 11, 2014

በመረብ ለኸ ወረዳ በጥቃቅንና ኣነስተኛ ድርጅቶች ተሰማርተው ለመስራት የመኮሩ በክፍተኛ ትምህርት ቤት የተመረቁ ወጣቶች በስራኣቱ ብልሹ ኣስተዳደር ምክንያት ችግር ላይ ወድቀው እንደሚገኙ ገለፁ፣



በትግራይ ምዕራባዊ ዞን መረብ ለኸ ወረዳ ራማ ከተማ የሚገኙ ወጣቶች በክፍተኛ ትምህርት ቤት ገብተው በድግሪና ዲፕሎማ ከተመረቁ በኋላ ከደረጃ ትምህርታቸው የሚመጣጠን ቀዋሚ ስራ በመንግስት ይሁን በግል ተቋማት ማግኘት ባለመቻላቸው። የኑራቸው ሂወት ለመምራት እንደ ኣማራጭ በጥቃቅንና ኣነስተኛ ድርጅቶች ውስጥ ተደራጅተው ለመስራት የጀመሩት እንቅስቃሴ። ካካባቢው መስተዳድር ከቃል ያለፈ ተግባራዊ  ድጋፍ ማግኘት ባለ መቻላቸው። ወደ ኪሳራ መግባታቸው ተገለፀ፣
  
     የወረዳውና የከተማው ኣስተዳዳሪዎች በጉልበታቹህ ለመስራት ብቻ ተነሱ እንጂ ለምታካሂዱት ስራ የሚያግዝ በቂ መሬት በመረጣቹሁበት ቦታ እንሰጣቹሃለን የሚል ቃል ከገቡላቸው በኅላ። በማህበር ተዳራጅተው ኣስር ኣስር ሺ ብር ከመንግስት ተበድረው የወተት ላሞች ገዝተው መንቀሳቀስ ቢጅምሩም ዉጤት ለማግኘት እንዳልቻሉና።  ቃል በተገባላቸው መሰረትም መሬቱ እንዲሰጣቸው ወዳካባቢው ፅፈት ቤት ተመልሰው በጠየቁበት ግዜም ጥያቂያቸው የሚያዳምጥ ኣካል ባለማግኘታቸው ምክንያት። የወተት ላሞቹ  በቂ ምግብ እጥተው በመሞት ላይ እንደሚገኙ የማህበሩ ሊቀ መንበር ሃፍቶም ታደሰ፤ ምክትሉ ሰላም ክብሮምና ፀሃፊው ኣድሃኖንም ገብረማርያም በኣስተዳደሩ ተታልለን ላልተፈለገ እዳ ተጋለጥን በማለት ምሬታቸው እንዳሰሙ መረጃው ኣክሎ ኣስረድተዋል፣