እነዚህ ለስሙ ብቻ የፀጥታ ኣስከባሪዎች
ተብሎው በከተማዋ የተሰማሩ የፖሊስ ኣባላት በታህሳስ 29/2006 ኣ/ም የከተማዋ ነጋዴዎች የልደት ኣመት በኣል ለማክበር ብሎው
የስራ ድርጅታቸውና መኖርያ ቤታቸው ዘግተው መሄዳቸው ካረጋገጡ ቦሃላ የማከፋፈያ መደብሮች፤ ሱቆችና መኖርያ ቤቶች እየሰበሩ በርከት
ያሉ ንብረትና ገንዘብ በመኪና ጭነው በመውሰድና ስውር ቦታ ላይ በመደበቅ፣ለግል ጥቅማቸው እንዳዋሉት ለማወቅ ተችለዋል፣
መረጃው ጨምሮ እንዳስረዳው በወቅቱ በጥበቃ ላይ በተሰማሩ ፖሊሶች ንብረታቸውና
ገንዘባቸው ከተሰርቁ ባለ ሃብቶች የተወሰኑት ለመጥቀስ።-
እምባሁን መሸሻ የሸቀጣ ሸቀጥ ነጋዴ፤ ሙክታር
መሃመድ ስኳርና ቡና ተቀምጦበት ከነበረ መደብሩ 9 ኩንታል፤ መስፍን መኳንንት 20 ኩንታል፤ ረዚቕ መሃመድ 10 ቦንዳ ልብስ የተወሰደባቸውና
ሌሎች ስማቸው ያልተገለፁ መኖራቸው ቢረጋገጥም። በወቅቱ በዝርፍያ ላይ ተሰማርተው ለነበሩ ፖሊሶች ለማስመሰል ሲባል ተገምግመው እንዲታሰሩ ቢደረግም፥ በሃላ ግን ያለምንም ማጣራት
እንደተለቀቁ የተገኘው መረጃ ገልፀዋል፣