እነዚህ ከተላያዩ የትግራይ ዞኖች የተሰበሰቡ ሴቶችና አካለ መጠን ያልደረሱ
በሺዎች የሚቆጠሩ እስረኞች ለእለታዊ ሂወታቸው የሚያስፈልጋቸው እንደ ምግብ፤ ውሃና የመሳሰሉትን ባለ ማግኘታቸው ምክንያት በተለያዩ
ተላላፊ በሽታዎች እየተሰቃዩና ህክምናዊ ርዳታ አጥተው በከባድ ችግር እንደሚገኙ የደረሰን መረጃ ገለፀ፣
በእስር ቤቱ የሚገኙ ክፍሎች ከመጠን በላይ በታሰሩ ዜጎች ተጥለቅልቀዋል
ያለው መረጃው። እስረኞቹ የሚተኙበት መሬት አጥተው እየተቀያየሩ ከፊሉ ቁጭ ሲል ሌሎቹ ቁመው እንዲያድሩ እየተገደዱ መሆናቸውና። በሌላ ተደራራቢ ችግር
ኣካላቸው ተጎሳቁሎ ለአደጋ ተጋልጠው እንደሚገኙ መረጃው አክሎ ኣስረድተዋል፣
ይህ ዓይነቱ ተግባር በዚህ ብቻ ሳይወሰን
በመላው የአገራችን ክልሎች እየተፈፀመ ያለ የአምባገነኑ የኢህአዴግ ገዢ መንግስት እኩይ ተግባር መሆኑን በተለያዩ አጋጥሚዎችን በዜና
እውጃችን እየገልፅነው መምጣታችን ይታወሳል፣