Saturday, January 25, 2014

ከሳውዲ አረብ የተመለሱ ኢትዮጵያውያን ዜጎቻችን በከፋ የኑሮ ደረጃ ላይ ወድቀው እንደሚገኙ ተገለፀ፣




በሃገራቸው ስራ በማጣት ምክንያት ሲሰቃዩ የነበሩ ወገኖቻችን ስራ ፍለጋ ወደ ሳዐውዲ አረብያ በተለያዩ ግዜ የተሰደዱ ኢትዮጵያውያን። ባሳለፍነው ወር የሳውዲ አረብ መንግስት ከኢህአዴግ መንግስት ጋር ባደረጉት ስደተኞችን ወደሃገራቸው የመመለስ ስምምነት ሩብ ሚሊዮን የሚሆኑ ኢትዮጵያውያንን የሳውዲ አረብ መንግስት በራሱ ወጪ ካገሩ ካባረራቸው በኋላ። በስልጣን ባለው የኢህአዴግ መንግስት ምንም አይነት ድጋፍ እንዳላገኙ የችግሩ ሰላባ የሆኑትን መሰረት በማድረግ የደርሰን መረጃ አመለከተ፣
    ከስደት የተመለሱት ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን እንደገለፁት፤ በሃገራችን ስልጣን ተቆጣጥሮ ያለው የኢህአዴግ መንግስት ከሳውዲ አረብ ለተመለሱ  ዜጎቻችን ካሉበት ክልል ተከታትሎ ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው ቃል የገባላቸው ቢሆንም፤ በተግባር ግን የት ወደቁ ብሎ የሚከታተል አካል እንደሌለና ከነበሩበት የስደት ሃገር ኑሮ የከፋ ሂወት እያሳለፉ እንደሆነ ጨምረው አስረድትዋል፣