በአስገደ ፅንብላ ወረዳ በተለይ አሎጌን
ቀበሌ የሚገኙ ወጣቶች በቀበሌያቸው የሚታረስ መሬት ይሁን ሌላ ስራ ሰርተው የግል ሂወታቸውንና ቤተሰቦቻቸውን የሚያስተዳድሩበት የስራ ዘርፍ ስለሌለ አጋጥሟቸው ላለው ከባድ
ችግር ለመፍታት ወደ ተለያዩ አካባቢዎችና ትላልቅ ከተሞች ሂደው ሰርተው የግል ሂወታቸውንና ቤተሰቦቻቸውን እንዳያግዙ በወረዳዋና
በቀበሌ አስተዳዳሪዎች ማስፈራርያና ማስጠንቀቂያ እየወረደባቸው እንደሚገኙ ለማወቅ ተችልዋል፣
በወረዳዋ የሚገኙ ወጣቶች በቀበሌያቸው
ሰርተው ዕለታዊ ሂወታችውን እንዲመሩና መብታቸው ተከብሮ የእርሻ መሬትና ሌላ የስራ እድል ለማግኘት በተደጋጋሚ ላቀረቡት አቤቱታ
መልስ ስላላኙ። የትውልድ ቀያቸውን በመተው ወደ ከተማ መፍለስ እንደአማራጭ
እየውሰዱት ላለው ውሳኔም ቢሆን። እንደወንጀል ተቆጥሮ እንዳይንቀሳቀሱ መከልከላቸው ሃዘን ውስጥ እንደከተታቸው መረጃው ጨምሮ አስረድትዋል፣
መረጃው በመጨረሻ ኢትዮጵያዊ ዜጋ
በሃገሩ ውስጥ ሰርቶ ሂወቱን ወደ ሚያስተዳድርበት ገጠር ይሁን ከተማ እንዳይሄድ የሚከለክል ህግ ባይኖርም ስርዓቱ ግን በሁሉም ክልሎች
ወጣቱ ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ እንዳይሰራና ሂወቱን እንዳይመራ ተከልክሎ እንደሚገኝ መረጃው አክሎ አስረድተዋል፣