በኣገር ደረጃ በተለይ ደግሞ በመቀሌ ከተማ ውስጥ በኣላቂ ነገሮች ላይ እየታየ ያለው የዋጋ መጨመር ሂደት
ኣስታክከው የከተማዋ ኣስተዳዳሪዎች ራሳቸው ለፈለግዋቸውና ለመረጥዋቸው ሰዎች በተለያየ ኣካባቢ የሸማች ማህበር እያሉ በማደራጀት
ከግብርና ሌሎች እዳዎች ነፃ ሆነው እንዲንቀሳቀሱ በመፍቀድና በቀላሉ ሊያገኙት የማይችሉት እንደ ሱኳር፤ ዘይትና የፍርኖ ዱቄት የመሳሰሉትን
እንዲያከፋፍሉ በማድረግ የማይገባቸውን ጥቅም እንዲያገኙ በማለት በር ከፍተውላቸው እንደሚገኙ ተገለፀ፣
የህወሃት ኢህኣዴግ መንግስት በተለያዩ
ጥቅሞች እየደለለ የስልጣኑ ማራዘምያ የሚሆኑት ሰዎችን በስፋት በመመልምል
ስራ ላይ እንዳለ የገለፀው መረጃው ባሁኑ ወቅት ለህዝቡ እለታዊ ኑሮ የሚውሉ እንደ ሱኳር፤ ዘይትና የፍርኖ ዱቄት የመሳሰሉት ኣላቂ
ነገሮች ጠቅልለው ከገበያ እንዲጠፉ በማድረግ። ራሱ ባደራጃቸው የስርኣቱ ወገን ኣባላት እንዲከፋፈል በማድረጉ ምክንያት። ነዋሪው
ሳይወድም ቢሆን የነሱ ተለጣፊና ኣባል እንዲሆን ለማድረግ ጥረት እያደረጉ መሆናቸው መረጃው ጨምሮ ኣስረድተዋል፣