Friday, February 21, 2014

በጎንደር ከተማ ውስጥ ሰማያዊ ፓርቲ የተባለው ተቃዋሚ ፀረ ህወሃት ኢህአዴግ ሰላማዊ ሰልፍ ባደረገበት ግዜ የስርዓቱ አባላት በሰልፉ ላይ ተሳታፊ እንደነበሩ ምንጮቻችን ከከተማዋ በላኩልን መረጃ ለማወቅ ተችልዋል።



በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ በሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪነት በጥር 25/2006 ዓ.ም ፀረ ህወሃት ኢህአዴግ የተመለከተ እጅግ ጠንካራና ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ እንደተካሄደ የገለፀው ይህ መረጃ በዚህ ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍም በርካታ የስርዓቱ አባላት ተሳታፊ እንደነበሩ መረጃው አስታውቅዋል።
ከከተማዋ የደረሰን መረጃ ጨምሮ እንደሚያሰረዳው በዚህ ደማቅና ጠንካራ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የጎንደር ከተማ ነዋሪ ህዝብ በብዛት መሳተፉ ተጨማሪ ድባብ ሆኖ እንደነበረና በተለይ ደግሞ በሰላማዊ ሰልፉ ላይ በነበሩ ወቅታዊ መፈክሮች ተማርከው በሰልፉ ላይ ከተሳተፉ የህወሃት ኢህአዴግ አባላት ውስጥ በስርዓቱ የፀጥታ ሓይሎች ታፍነው ዳብዛቸው የጠፉ እንዳሉ መረጃው አክሉ አስረድትዋል።
በመጨረሻ በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ በመካፈላቸው በህወሃት ኢህአዴግ የፀጥታ ሃይሎች ታፍነው ከተወሰዱት ሰዎች መካከል፣ አምሳ አለቃ ታምራት ጌታሁን ከዚህ በፊት ወታደር የነበረ፤ ካህሱ አስራት ፤መምህር አለም ፈንታሁንና ተማሪ መቅሰም ረታ የተባሉ የሚገኙባቸው ሲሆኑ። እነዚህ ሰዎች ለምን በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ተገኛችሁ እያሉ ሲያንገላትዋቸው ከቆዩ በኋላ አፍነው ወዴት እንደወሰድዋቸው የሚታወቅ ነገር እንደሌለ በችግሩ ሰለባ የሆኑትን ቤተሰቦች መሰረት በማድረግ ከጎንደር ከተማ የደረሰን መረጃ አስገነዘበ።