Friday, February 21, 2014

በአውደራፊእ ሰላማዊ ህዝብ ላይ ግፍና በድል ሲፈፅሙ የነበሩ የፖሊስ አባላት ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች እንደተገደሉ ከቦታው በደረሰን በረጃ ለማውቅ ተችልዋል።



በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ሁመራ ወረዳ በአውደራፊእ ከተማ ለሚኖር ህዝብ የተለያዩ ምክንያት እየፈጠሩ በሰላማዊ መንገድ ኑሮውን እንዳይመራ ሲያንገላቱት የቆዩ ሁለት የኢህአዴግ መንግስት የፖሊስ አባላት ጥር 28/2006 ዓ.ም ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ማንነታቸው ባልታውቁ ሰዎች በእጅ ቦንብ እንደተገደሉ የተገኘው መረጃ አመለከተ።
እነዚህ የተገደሉ የፖሊስ አባላትም ዋና ሳጅን ይታገሱና ኮንስታብል መኳንንት የተባሉ ሲሆኑ በአገዳድሉ የተደናገጡ የስርዓቱ ካድሬዎችም ለአካባቢው ነዋሪ በአይነ ቁራኛ በማየት ቁጥራቸው ጥቂት የማይባሉ ዜጎችን አስረው በማሰቃየት ላይ እንደሚገኙ መረጃው ጨምሮ አስረድትዋል።