በአማራ ክልል አብደ
ራፍዕ አካባቢ በእርሻ ስራ ላይ እየሰሩ ካሉ ባለሃብቶች አቶ ጸጋይ መድሃንየ እንደሆነ የገለጸው መረጃው ይህን ባለሃብት የዞኑና
የወረዳው የአስተዳዳሪዎችን ፍላጎት ስላላሟላ በሰላዮቹ አማካኝነት ጥብቅ ክትትል በማድረግ እርሻው ውስጥ የሚሰሩ የቀን ሰራተኞች
የተቃዋሚ ድርጅት አባላት መሆናቸውን እያወቅክ ደብቀህ እያሰራሃቸው ነህ ብለው በሓሰት በመፈረጅ ስያስፈራሩት ከቆዩ በኃላ የሰው
እንቅስቃሴ በሌለበት ሰአት የካቲት 17 2006 ዓ/ም የእርሻ ካምፑን
በእሳት እንዳጋዩት ለማወቅ ተችለዋል።
መረጃው በማስከተል ቃጠሎው በመከሰቱ ምክንያት ለሰራተኞች ተብሎ የተዘጋጀው
15 ኩንታል ዱቄት፤ 3 ጀሪካል የምግብ ዘይት፤ ሁለት የትራክተር ማረሻ፤ ሌሎች በርከት ያሉ እቃዎች አብሮው እንደተቃጠሉና ይህ
በስርአቱ ባለ-ስልጣናት ፖለቲካዊ ሰበብ አቶ ጸጋይ በተባለው ንፁህ ዜጋ ላይ የደረሰው ግፍ ስልጣን በመጠቀምና በማስፈራራት ገንዘብ
ለመዝረፍና ግላዊ ጥቅማቸውን ለሟሟላት ሲሉ ያደረጉት ተንኮል እንደሆነ መረጃው አክሎ አስረድተዋል።