በናዕዴር ዓዴት ወረዳዎች
ላይና ታች ማይጨው በተባሉ ቦታዎችና ጭላ ኣካባቢ ሲኖሩ ቆይተው በማህበራዊ ችግሮች ሳብያ ወደ ከተማ የገቡ አባወራዎች ህጋዊ የእርሻ
መሬታቸው በስርአቱ አስተዳዳሪዎች እየተነጠቀ ጉቦ ለሰጡዋቸው ከተማ ውስጥ ለሚኖሩ ባለ ሃብቶች እያከፋፈሉት በመሆናቸው አርሶ አደሮቹ
የካቲት 18 ቀን 2006 ዓ/ም ተቃውማቸውን እንዳሰሙ ለማወቅ ተችለዋል።
እነዚህ
በዞኑ አስተዳዳሪዎች ላይ በሰላማዊ ሰልፍ ተቃውሞአቸውን የገለፁ ከ 250 በላይ የሚገመቱ አርሶ አደሮች ባካሄዱት ተቃውሞ
ላይ “ መሬት በጉቦ እየተከፋፈለ ነው፤ ድሃው ወገን የሚሰማው ሰው አጣ፤ ሃብታም በገንዘቡ እንዲጠቀም በመደረጉ ምክንያት ፍትሃዊ
አሰራር እንዲዛባ ተደረገ፤ እትብታችን በተቀበረበት መንደር ጥገኛ ሆነን እንድንኖር ተፈረድን” በማለት በስርአቱ ላይ ያላቸውን ጥላቻ
መግለፃቸውና ይህ ተግባርም በሁሉም የትግራይ አካባቢዎች በሰፊው እየተሰራበት ያለ ኢ-ፍትሃዊ ድርጊት መሆኑን መረጃው አክሎ አስረድተዋል።