Thursday, March 27, 2014

በአዲስ አበባ ከተማ ክፍለ ከተማ ካሳንችስ ውስጥ በማህበር የተደራጁ የትግራይ ተወላጆች የሆኑ የቀድሞ ተጋዮች የካቲት 11 የሂወት መስዋእትነት ከፈልንላት እንጂ ያገኘንላት ካሳና ጥቅም የለም በማለት በስምዋ ያካሄዱት ግብዣ ይሁን ሰልፍ እንደሌለ ታወቀ።



   ለበርካታ አመታት ከህወሃት ጎን ተሰልፈው ሲታገሉ ደማቸውና አጥንታቸው የከሰከሱ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ታጋዮች በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የህወሃት ጽሕፈት ቤት የካቲት 11 አስመልክተው ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያደርጉና ለበአሉ ዝግጅት የሚሆን የገንዘብ መዋጮ እንዲያሰባስቡ በተጠየቁበት ግዜ የካቲት 11 ለኛ ከጥር 11 የሚለያት ምንም ምክንያት የለም፤ እኛ የታገልነው ለህዝብ ጥቅም፤ ሰላምና ብልፅግና እንጂ ተመልሶ ወደ ስቃይና አፈና እንዲገባ አልነበረም። በመሆኑም በማህበራችን ይሁን በግላችን ህወሃትን ለመደገፍ ተነሳሽነት የለንም ብለው እንደተናገሩ ከአዲስ አበባ ከተማ የተገኘው መረጃ አስታወቀ።
    እነዚህ የቀድሞ የህውሃት ታጋይ አባላት በመታገላችን በስርአቱ እንደ ተጠርጣሪዎችና ጠላቶች ታይተን በተወለድንበትና ባደግንበት አካባቢ እንኳን ሰርተን ለመኖር ስላልቻልን ቦታ ቀይረን ለመኖር ተገደናል ድሮ ትግል ውስጥ እያለን የምናውቀው ህወሃትና አሁን በስልጣን ላይ ያለው ህወሃት ፍፁም የማይገናኙ ሁለት ጫፎች በመሆናቸው በአሁኑ ግዜ ለህወሃት መደገፍ አስፈላጊነት የለውም በማለት ተቃውማቸውን እንደገለፁና ከነዚህም ለተብርሃን ክፍለ ( ጓል ሕንጣሎ ) አንድዋ እንደሆነች መረጃው አክሎ አስረድተዋል።