Sunday, March 23, 2014

በትግራይ ምራባዊ ዞን ሁመራ ከተማ በሚገኝ ፖሊስ ጣብያ በርከት ያሉ ወጣቶችን ባልዋሉበት ወንጀል ታስረው እየተሰቃዩ እንደሚገኙ ምንጮቻችን ከአካባቢው ገለፁ።



   በደርሰን መረጃ መሰረት ከተለያዩ የሃገራችን አካባቢዎች ሁመራ በሚገኘው ሰፊ የእርሻ መሬት ሰርተው ዕለታዊ ኑሮአቸውን ለመምራት የሄዱ ወጣቶች የወረዳዋና የዞኑ የፀጥታ ሃላፊዎች ባሰማርዋቸው ተላላኪ ካድሬዎች ከሚውሉበትና ከሚያድሩበት ቦታ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ተወስደው በእስር ላይ እንደሚገኙና እነዚህ የታሰሩ ዜጎችም  የሚያያቸው አካል አጥተው በከባድ ችግር ላይ እንደሚገኙ ታውቀዋል።
    እነዚህ ባልዋሉበት ወንጀል ታስረው እየተሰቃዩ ያሉ ወገኖች አብዛኛዎቹ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተምርቀው ሥራ ያጡና ከሌላው የህብረትሰብ ክፍልም እንደሚገኙባቸው የገለፀው ይህው መረጃ  ተመራቂዎቹ የቤተሰብ ሸክም ከመሆን ብለው እንዳማራጭ የጉልበት ስራ ሰርተው ራሳቸውን ለመቻል ወደ ሁመራ በተንቀሳቀሱበት ወቅት እናተ በዚህ መንግስት እምነት ስለሌላችሁ የትጥቅ ትግል ከሚያካሄዱ ድርጅቶች ጋር እየተገናኛችሁ መረጃ ለመስጠትና ከነሱም ተቀብላችሁ ለህዝቡ በመንገር ህዝቡ ፀረ መንግስት እንዲነሳ ለማድረግ የመጣችሁ ናችሁ በማለት ምንም አይነት ጭብጥ በሌለው ጥርጣሬ ያለምንም የፍርድ ቤት ወሳኔ ለወራት ስለታሰሩ ቤተሰቦቻቸው በዚህ አይኑን ባፈጠጠ የሃሰት ጥርጣሬ ለታሰሩት መፍትሄ እንዲደረግላቸው ወደሚመለካታቸው አካላት ላቀረቡት ተደጋጋሚ ጥያቄ ሰሚ እንዳጡ መረጃው አስረድትዋል።
    ከወረዳው ሳንወጣ ማይካድራ በተኪኤ ባህታ የእርሻ ቦታ የሚሰሩ ሰራተኞች ተሻለ በተባለ ሚሊሻ ለአንዲት ሴት ወሽመሃታል ብላችሁኛል በሚል ሰንካላ ምክንያት በየካቲት 28/2006 ዓ.ም ለአራት ሰራተኞች ገድሎ ሌላ አንድ ካቆሰለ በኋላ መጨረሻ ላይ ሂወቱን በገዛ እጁ በራሱ መሳርያ እንደገደለ ምንጮቻችን በላኩት መረጃ ለማውቅ ተችላዋል።
    ይህ በእንዲህ እንዳለ በስልጣን ላይ የሚገኘው ስርዓት በንፁሃን ዜጎቻችን ላይ የተፈፀመውን አስነዋሪ ድርጊት ወደ ህዝብ እንዳይሰራጭ በመፍራት በወረዳዋ የሌለና ያልተሰራውን የመሰረት ልማት ማለት እንደ ኤሌክትሪክና ንፁህ የመጠጥ ውሃ በሌለበት ለማይካድራ ህዝብ እየጠቀማቸው እንዳለ ለመምሰል በታጣቂዎቹ እየተድረገ ያለውን ሰላማዊ ሰዎችን የማሸበርና የመግደል ተግባር ለመደበቅ ሲል በሚዲያው አድርጎ እያሰራጨ ያለው ሃቅነት ያለተላበሰ ወሬ የወረዳዋ ነዋሪዎችን እንዳበሳጫቸው ከቦታው የተገኘው መረጃ አክሎ አስረድተዋል