Sunday, March 23, 2014

የአዊ ዞን አመራሮች መንግስትን በመቃወም የትጥቅ ትግል የሚያካሂድ “ የአዊ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ” የተባለ ድርጅት አለ በማለት ከገጠር ወደ ከተማ ለሚገባ ማንኛውም ሰው በጥርጣሬ አይን ታይቶ እንዲፈተሽና እንዲያዝ ጥብቅ መመርያ ማስተለለፋቸው ተገለፀ።



በመረጃው መሰረት የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች በአማራ ክልል ውስጥ የአዊ ዞን ፀጥታ ሃላፊ የሆነው ምናለ የተባለ የስርአቱ ቅጥረኛ የአዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በሚል ስያሜ የሚንቀሳቀስ የሰማያዊ ፓርቲ አካል በዞኑ ወስጥ አለ በማለት ማንኛውም ከገጠር ወደ ከተማ የሚንቀሳቀስ ሰው ህጋዊ እንዳልሆነ ታውቆ ተይዞ እንዲጠየቅ ትእዛዝ በመተላለፉ ምክንያት ነዋሪው ህዝብ በከፍተኛ ውጥረትና ጭንቀት ላይ መሆኑን የተገኘው መረጃ አስታወቀ።
    ይህ በእንዲህ እንዳለ በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ውስጥ ኢንቨስት ለማድረግ የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን የግል ባለሃብቶች ከክልላቹህ ውጭ ምን ለማድረግ መጣቹሁ እየተበሉ አገራቸው ውስጥ ሰርተው እንዳይኖሩ እይተባረሩ መሆናቸው ተገለፀ።
    እነዚህ የግል ባለሃብቶች ራሳቸው ጠቅመው ህዝቡንና አገሪቱን ለመጥቀም በማለት ማንቡክ፤ አልሙ፤ መንደር ሰባት፤ ግልገል በለስና ሌሎች የክልሉ አካባቢዎች ሃብታቸውን አፍስሰው ለመስራት ቢሞኩሩም የጀመሩት የልማት ስራ አቋረጦው እንዲወጡ በማሰብ  የአከባቢው ባለስልጣናት በአካባቢያችን የተቃዋሚ ድርጅቶች ጫና ስላለ ወደ ክልላቹህ ሂዱ ተብሎው በስርአቱ መስተዳድር አስገዳጅነት ባለሃብቶቹ ከቦታው እየለቀቁ መሆናቸው ለመረዳት ተችለዋል።
   ብስርአቱ አስገዳጅነት ከቦታው ከተባረሩት ባለሃብቶች መካከል የአዊ ብሄረሰብ ተወላጆች መኖራቸውም የገለፀው መረጃው እየደረሰባቸው ባለ ኪሳራና እንግልት መፍትሄ እንዲደረግላቸው ወደ ሚመለከታቸው የስርአቱ ባለስልጣናት ላቀረቡት ጥያቄም በአካባቢያችን የተቃዋሚዎች ጫና በመኖሩ ምክንያት ከክልላቹህ ውጭ መጥታቹህ ማልማት አትችሉም የሚል መልስ እንደተሰጣቸውና ሳይወዱ ተገደው እንዲወጡ እየተደረገ መሆኑን። ውስጥ አዋቂዎች ከቦታው አስታውቀዋል።