Thursday, March 20, 2014

በወንበርማ ወረዳ የሚገኙ የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች የብአዴን ኢህአዴግ ድርጅት አባላት እንዲሆኑ የቀረበላቸው ጥያቄ እንዳልተቀበሉት ምንጮቻችን ከቦታው አስታወቁ።



    በአማራ ክልል ምእራብ ጎጃም ዞን፤ ወንበርማ ወረዳ በሚገኙ 46 የጤና ኤክስተንሽን ውስጥ ተመድበው እየሰሩ ያሉ ባለሙያዎች የብአዴን ኢህአዴግ አባላት እንዲሆኑ በተጠየቁበት ግዜ ማንነታችን ነው የምትፈልጉት ወይስ ገንዘባችን በማለት አብዛኛው የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኛ እንዳልተቀበለውና ቀደም ብሎው የድርጅቱ አባል ከሆኑትም ኣብዛኛዎቹ የአባልነት መዋጮ ለመክፈል ፍቃደኞች እንዳልሆኑ ለማወቅ ተችለዋል።
    መረጃው በማስከተል ሰራተኞቹ በስርአቱ የበላይ ካድሬዎችና አመራሮች ጉዳት እንዳይደርስባቸው በመስጋታቸው ምክንያት ቀደም ብለው የድርጅቱ አባላት ከሆኑት 11 ሰራተኞች ውስጥ ስድስቱ ብቻ አመታዊ የአባልነት መዋጮ ሲከፍሉ አምስቱ ያለመክፈላቸው በድርጅቱ ውስጥ ተፈጥሮ ያለው ያለመተማመንና የመከፋፈል ሁኔታ የሚያሳይ ነው ሲሉ አንዳንድ የብአዴን አባላት እንደመነጋገርያ እየተጠቀሙበት መሆናቸው ምንጮቻችን ከወንበርማ ወረዳ ገለፁ።
    ይህ በእንዲህ እንዳለ ስልጣን ላይ ያለው የወያኔ ኢህአዴግ ስርአት በስሩ በሚገኙ አራቱ ድርጅቶች በብአዴን፤ ህወሃት፤ ኦህዴድና ደኢህዴግ መንገድ ተጠቅሞ። በተለያዩ የመንግስት መስራቤቶች በሚገኙ ሰራተኞች ላይ የተለያዩ ጫናዎች በመፍጠር የስልጣኑ እድሜ የሚያራዝሙ ብዛት ያላቸው አባላት ለማፍራት አቅዶ ላይና ታች እያለ ቢሆንም። እየተከተለው ባለው ፀረ ህዝብ መንገድ ቅር የተሰኙ ሰራተኞች  የኢህአዴግ አባላት ከመሆን የሌሎች ተቃዋሚ ድርጅቶች አባላት መሆን እንደሚሹ መረጃው ጨምሮ አስታውቀዋል።