Monday, March 31, 2014

በሁሉም የአማራ ክልል ዞንና ወረዳዎች የሚኖረው ህዝባችን ለመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን የሚውል ገንዘብ ብግድ እንዲከፍል እየተገደደ መሆኑ ከቦታው የደረሰን መረጃ አስታወቀ።



በአማራ ክልል የሚኖሩ ወገኖች እያንዳዱ አርሶ አደር አንድ መቶ ብር ለመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን የሚውል ገንዘብ እንዲከፍል እየተገደደ መሆኑን የገለፀው መረጃው በተለይ የበታች አስተዳዳሪዎች በስርአቱ ተቀባይነት ለማግኘት ሲሉ ከተመደበው መጠን ገንዘብ በላይ ህዝቡን እያስከፈሉት መሆናቸው  መረጃው አስታውቀዋል።
     መረጃው በማስከተል ለወረደው መመርያ ተግባራዊ ያላደረገና ለመክፈል አቅም የለኝም ያለ ወገን እየታሰረ መሆኑንና ከታሰረ በኋላም የኋላ ታሪኩ መጠናት አለበት እየተባለ፣ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ የተቃዋሚ ድርጅት አባልና በፀረ ልማት ስራ ላይ የተሰማራህ ነህ እየተባለ በላዩ ላይ በደል እየተፈፀመበት መሆኑ ያስረዳል።
    እነዚህ ለመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን ገንዘብ አላዋጣቹሁም ተብሎው እየታሰሩ ያሉ ዜጎቻችን ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዳይገናኙና እንዲጨነቁ በማድረግ ለተጠየቁት ገንዘብ እንዲከፍሉ የሚያስችል ጫናዎች እየፈጠሩባቸው እንደሆነ መረጃው ጨምሮ አስረድተዋል።