Monday, March 31, 2014

በአማራ ክልል በላያ፤ አዊ፤ ዋግ-ኽምራ በተባሉ ዞኖችና ኩንፋ በተባለው አካባቢዎች የሚገኙ ዜጎች እንደ ክልል እንድንታወቅ መብታችን ይከበርልን ሲሉ መናገራቸው ምንጮቻችን ከክልሉ አስታወቁ።



በመረጃው መሰረት በአማራ ክልል የሚገኙ የህምፀንና የአገውን ቋንቋ ተናጋሪ ወገኖች አ.ብ.ዴ.ፓ የሚል ድርጅት መስርተውና በብሄራቸው ተደራጅተው እንደ አንድ ክልል እንዲታወቁና  መብታችው እንዲከበርላቸው በማለት ወደ ሚመለከታቸው አካላት ላቀረቡት ጥያቄ ያካባቢው ባለስልጣናት ተገቢ መልስ እንዳልሰጡበት ለማወቅ ተችለዋል።
     መረጃው በማስከተል የመንግስት ባለ-ስልጣናቱ በበላያ፤ አዊ፤ ዋግ ኽምራ ዞንና በኩንፋ ኣከባቢ ነዋሪዎች ውስጥ ጣልቃ በመግባት የመብት ጥያቄ ላነሳው ህዝብ እንደ አንድ ፀረ ሃገርና መንግስት አስመስለው በማቅረብና ለካድሬዎቻቸው ሰብስበው በመግለፅ የመብት ጥያቄ ባነሱት ንፁሃን ወጎኖቻችን ላይ ጥያቄያቸውን እስኪቀይሩ ድረስ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ መመርያ እንደሰጥዋቸው ታውቋል።
     በመጨረሻ የአማራ ክልል ባለስልጣናት ባደረጉት ስብሰባ ላይ ተቃውሞ ሊያሰሙ ይችላሉ ለተባሉት የበላያ፤ አዊ፤ ዋግ ኽምራና ኩንፋ አካባቢ በህብረተሰቡ መሃል ለሚገኙ ሴት የካብኔ አባላት በሚቀርበው የህዝብ ጥያቂ ላይ እገዛ ያረጋሉ በሚል ምክንያት በቀን 500 ብር አበል እየተሰጣቸው ስብሰባው ውስጥ እንዲካፈሉ እንደተደረገ መረጃው አክሎ አስረድተዋል።