Monday, March 31, 2014

በምእራብ ጎጃም ዞን ወንበርማ ወረዳ ውስጥ የሚገኙ አርሶ አደሮች፣ ከአቅማቸው በላይ ግብርና የማዳበርያ ብድር ወለድ እንዲከፍሉ በመደረጉ ምክንያት ለረሃብና ኪሳራ መጋለጣቸው ተገለፀ።



በመረጃው መሰረት አርሶ አደሮቹ ክፈሉት የተባሉት ግብር ከሚያገኙት ገቢ ጋር የማይመጣጠን በመሆኑና በአካባቢው መስተዳድር ተገደው እንዲወስዱት የተደረገ የማዳበርያ ብድር ወለድ ከፍተኛ ስለሆነ ብዙ ወገኖች በሁኔታው ተማረው ቀያቸውን ለቀው እየጠፉ መሆናቸው የተገኘው መረጃ አስታወቀ።
     ተመጣጣኝ ባልሆነውና ከአቅማቸው በላይ በሆነው ግብርና ወለድ መክፈል ተስኖዋቸው ቤተሰባቸውን ይዘው ከቦታው ከጠፉት አባዎራዎች አንዱ የሆኑት አቶ አበባው ዮውሃንስ የተባሉት ግለሰብ 47 ሺ የመዳበርያ ብድር እዳ አለህ በመባላቸው ምክንያት ይህን ሁሉ እኔ የተጠቀምኩበት አይደለም በማለት ተደናግጠው ቦታቸውን ለቀው እንደተሰወሩ ለማወቅ ተችለዋል።
     ይህን የስርአቱ ብልሹ አሰራር ንፁሃን ወገኖቻችን አገራቸውን ለቀው እንዲሰደዱና እንዲጠፉ ምክንያት መሆኑንና አሁንም በሁኔታው አስከፊነት ጉዳዩ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ መሄዱ መረጃው አክሎ አስረድውተዋል።