Sunday, March 23, 2014

በተለያዩ የሰራዊቱ ክፍል የሚገኙ የትህዴን ሴት ታጋዮች አህጉራዊ የሴቶች በአል / march 8 / አስመልክተው ደማቅ በአል እንዳደረጉ ተገለፀ።



ይህ በአለም አቀፍ ደረጃ ለ104 ግዜ የተከበረው በአል በትህዴን ሴት ታጋዮችም ከ2001 ዓ/ም ጀምሮ በየአመቱ እየተከበረ እንደመጣና ዘንድሮም የድርጅቱ ኣባላትና አመራሮች በተገኙበት ለስድስተኛ ግዜ በከፍተኛ ደረጃ እንደተከበረ ለማወቅ ተችለዋል።
    በእለቱ በትህዴን ሴት ታጋዮች የቀረበው ፅሁፍ የኢትዮጵያ ሴቶች በተለይም የትግራይ ሴቶች ባለፉት ስርአቶች ሴቶች የቤት እመቤት ሆነው እንዳንድ ማህበራዊ ስራ ከመስራት ውጭ ሌላ ቁም-ነገር መስራት እንደማይችሉና ወደ አደባባይ ሳይወጡ በወንዱ የባላይነት ትእዛዝ ብቻ እንዲመሩ የሚያደርግ ስርአት በመሆኑ ምክንያት ባላያቸው ላይ ሲፈፅም የነበረ ግፍና በደል ለማብቃትና መብታቸውና እኩልነታቸው ለማረጋገጥ ሲሉም ለ17 ዓመታት ያህል በተካሄደው መራራ የትጥቅ ትግል ወቅት ክቡር ሂወታቸው ከፍለዋል ካለ በኋላ በማስከተል--የህወሓት ኢህአዴግ መሪዎች ግን ሴት በመሆናቸው ብቻ በላያላቸው ላይ ያለው ችግር ተቋቁሞው ደከመን ሰለቸን ሳይሉ ከነሱ የሚጠበቅ አኩሪ ገድል ፈፅመው ወደ ድል ከደረሱ በኋላ ድካማቸውና መስዋእትነታቸው ለጥቂት ባለስልጣናት አጨብጫቢዎች ሆኖ በመቅረቱ ምክንያት በፊት የተጀመረውን ትግል መጨረሻው ላይ ለማድረስና የበፊቶቹን ፈለግ አንግበው ጨቋኙ የወያኔ-ኢህአዴግ መንግስት ገርስሰው መብታቸው ለማረጋገጥ አሁንም ከትህዴን ጎን በመሆን ትግላቸው እያካሄዱ  ናቸው።