Sunday, March 23, 2014

የህወሓት ኢህአዴግ ባለ-ስልጣናት የአፅረጋን ህዝብ ሳያማክሩ ወደ ሸራሮ ከተማ የዘረጉት የውሃ መስመር ተቃውሞ እንዳስነሳ ምንጮቻችን ከቦታው አስታወቁ።



በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን ታህታይ አድያቦ ወረዳ ልዩ ቦታ አፅረጋ ከሚገኘው አካባቢ የስርአቱ አስተዳዳሪዎች ህዝቡን ሳያማክሩ የውሃ መስመር ለመዘርጋት አስበው ስራውን በመጀመራቸው ምክንያት ህብረተሰቡ ውሃውን ያካባቢው ሃብት መሆኑ እየታወቀ ለምን በቅድሚያ በውስጣችን ያለው የውሃ እጥረት እንዲፈታ አልተደረገም? መንግስት በቅድሚያ ከኛ ጋር ሳይነጋገር የውሃ መስመር መዘርጋቱ በኛ ላይ ያለው ንቀት የሚያሳይ ነው በማለት ለተዘረጋው የውሃ መተላለፍያ ቱቦ በመጥረቢያ ቆራርጦው ከስራ ውጭ እንዳደረጉት ከቦታው የደረሰን መረጃ ገለጸ።
    በወቅቱ ለተነሳው የህዝብ ተቃውሞ የዞኑና የወረዳው አስተዳዳሪዎች ሊያረጋጉት ባለመቻላቸው ከክልል ተጠርተው የመጡ የበላይ ባለስልጣናት ለአፅረጋ ህዝብ ሰብስበው ለእንስሳዎቻቹህ ውሃ መጠጫ የሚሆን የውሃ ገንዳ እንሰራላቹሃለን በማለት ሁኔታውን ለማብረድ ቢሞኩሩም የአካባቢው ህብረተሰብ ግን ሁሌ በምትገቡልን አስመሳይ ቃል እየተታለልን አንኖርም እናንተ ቃል የምትገቡት የምትፈልጉትን እስክትወስዱ መሆኑን እናውቃለን በማለት የተጀመረው ስራ እንዲቆም ማድረጋቸው ለማወቅ ተችለዋል።
    ወዲ አወጣሽ የተባለ የሸራሮ ከተማ አስተዳዳሪ መጀመርያውኑ የአካባቢው ሽማግሊዎችና ታዋቂ ሰዎች በማገናኘትና ተማምነው ስራውን እንዲጀምሩት ያለመደረጉ እኛ እናውቅላቹሃለን የሚለው የስርአቱ የንቀት አካሄድ እንደሆነና ይሀውም ለአፅረጋና ሸራሮ ህዝብ ወዳልተፈለገው ፀብ በማስገባት በአይነ ቁራኛ እንዲተያዩ ተብሎ የተቀየሰ ሰይጣናዊ ተንኮል መሆኑ መረጃው አክሎ እስረድተዋል።
    ይህ በእንዲህ እንዳለ በሸራሮ ከተማ ውስጥ የተለያዩ የግል ድርጅቶች የመንግስት ግብር አልከፈላችሁም በሚል ምክንያት እየታሸጉ መሆነቸውና ከነዚሁም፣-
-     አቶ ታደሰ የፕላኔት ሆቴል ባለቤት፤
-     አቶ ፍቃዱ ባለ ሬስቶራንት፤
-     ወ/ሮ መብራት ባለመጠጥ ቤትና ሌሎች ያልተገለፁ የሚገኙባቸው እስካሁን ድረስ ድርጅታቸው ታሽጎ እንደሚገኝና አሁንም ይህ የማሸግ ድርጊት እየቀጠለ በመሆኑ ምክንያት ነዋሪዎቹ ከመጠን በላይ ለሆነው የግብር አከፋፈል ስርአት ማቆምያ እንዲበጅለት በመጠየቅ ላይ እንደሆኑ የደረሰን መረጃ አስታውቀዋል።