Tuesday, April 1, 2014

በመረብ ለኸ ወረዳ ውስጥ በትግሉ ወቅት ለተሰው ታጋዮች ተብሎ የተሰጠው መሬት በአስተዳዳሪዎች ተነጥቆ ለሌሎች ለመከፋፈል በተጀመረበት ግዜ በተነሳ ብጥብጥ 3 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ።



ብትግራይ ማእከላዊ ዞን መረብ ለኸ ወረዳ አሕሰአ በተባለው አካባቢ የሚገኙ የወያኔ ኢህአዴግ አስተዳዳሪዎች ከሰማእታት ቤተሰብ የእርሻ መሬታቸው ነጥቀው ለሌላ ለመስጠት በሞኮሩበት ግዜ አባቶቻችና ልጆቻችን እጥተን በድህነት ማቅ መኖራችን ሳይበቃ አሁን ደግሞ ሰማእት በሆኑ ስም የተሰጠችን ቁራጭ መሬት ለመውሰድ ተነሳቹህ በማለት በተነሳው የተቃውሞ ብጥብጥ የሰው ሂወት እንደጠፋ የተገኘው መረጃ አስታወቀ።
      የወረዳው አስተዳዳሪዎችና የሚልሻ አባላት በጥቅም ተሳስረው የሰማእታትን መሬት በድንገት ነጥቀው ለመከፋፈል በተነሱበት ግዜ የሰማእታት ቤተሰቦች ትልቅ ስሜት ውስጥ በመግባት “ የሰማእታት ካሳ እንዲህ ሆነ” በቃ ተረስተው መቅረታቸው ነው? ደማቸውና መስዋእትነታቸው በህወሃት ደመ ከልብ ሆኖ መቅረቱ ነው? በማን መስዋት ነው ለዚህ ስልጣን የበቃቹህ! በማለት ህዝቡ መሬቱን ለሌሎች ሰዎች ለመስጠት ከመጡት ተላላኪዎች ጋር ባካሄደው ብጥብጥ አንድ ከሰማእታት ቤተሰብ ሲሞት የስርአቱ ተላላኪዎች የሆኑ የቀበሌው የመሬት አስተዳዳሪ ገብረመድህን ተክሌና የቀበሌው ስራ አስከያጅ ተስፋ ሙሉጌታ እንደመቱ ለማወቅ ተችለዋል።
     መረጃው እንደገለጸው በወቅቱ በወያኔ ኢህአዴግ ስርአት ጥቅም ተደልሎ የሰማእታት መሬት ለማከፋፈል ሲሯሯጥ ለነበረው ካድሬ ገድሎ ለራሱ ሂወቱን ያጠፋው ግለሰብ በትግሉ ግዜ ክቡር መስዋእትነት ለከፈለው የታጋይ አታላይ መሃሪ ወንድም መሆኑ ለማወቅ ተችለዋል።