መረጃው እንደጠቆመው በወልቃይት ወረዳ እየተሰራ ለሚገኘው ስኳር ፋብሪካ እንዲዉል ተብሎ ከህዝብ የተሰበሰበ
ገንዘብ ለታለመለት አላማ ሳይዉል በባለስልናት እና የተቋሙ ስራ አስከያጆች ለግል ጥቅማቸዉ እያዋሉት መሆናቸው በመግለፅ የህዝቡ
ገንዘብ እያጠፋፉ ከሚገኙ አንዱ ደግሞ የፋብሪካው የተክኒክ ሃላፊ አቶ ፀጋይ ፍትዊ መሆኑን ታውቋል።
አቶ ፀጋይ ፍትዊ በፋብሪካው የቴክኒክ ሃላፊ ሁኖ እየሰራ ባለበት ግዜ ለተቋሙ
ስራ ማስከጃ ተብሎ የተመደበ ገንዘብ በመስረቅ በሸራሮ ከተማ መናሃርያ አካባቢ ደረጃው የጠበቀ ቪላ ቤት እየሰራ እንደሚገኝ እና
ይህ ደግሞ ብቻዉን ሳይሆን በስራዉ የሚገኙ ለፕሮጀክቱ እያስተዳደሩ ያሉ ሃላፊዎች የህዝቡ ገንዘብ እየሰረቁ ለግል ጥቅማቸው እያዋሉት
እንደሚገኙ ያገኘነው መረጃ አስታወቀ።
አቶ ፀጋይ ፍትዊ እየገነባዉ የሚገኝ ደረጃው የጠበቀ ቪላ የታዘቡ የሸራሮ
ከተማ ነዋሪዎች ከድሃው ህዝብ ለመሰረተ ልማት ተብሎ የተሰበሰበ ገንዘብ የስርአቱ አስተዳዳሪዎችና ተላላኪዎች ለግል ጥቅማቸው እያዋሉት
የሚገኙበት ምክንያትም የስርአቱ አስተዳደር በሙስና የተጨማለቀ መሆኑ የሚያሳይ ነው ሲሉ የተለያዩ ወጎኖች በምሬት አስተያየታቸዉን
እየሰጡ መሆናቸው ያገኘነው መረጃ ጨምሮ አስረድተዋል።