Tuesday, April 1, 2014

በአዲስ አበባ ከተማ ክፍለ ከተማ ቀራንዮ የሚገኙ አስተዳዳሪዎች ከህዝቡ የተዋጣ ገንዘብ ይዘው የጠፉ መሆናቸው ከከተማው የተገኘው መረጃ አስታወቀ።



በመረጃው መሰረት የቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳዳሪዎች በየካቲት 17/ 2006 ዓ/ም ለአካባቢው ህዝብ በመሰብሰብ መሬት ልንሰጣቹህ ስላሰብን በመደራጀት እያንዳዳቹህ 2,500 ብር ክፈሉ በማለት ከህዝቡ የሰበሰቡት 150 ሺ ብር ይዘውት እንደጠፉ ለማወቅ ተችለዋል።
    መሬት እንዲሰጣቹሁ ገንዘብ አዋጡ በማለት 150 ሺ ብር ከህብረተሰቡ ነጥቀው የጠፉ አቶ ጌታቸው ለማ የወረዳዋ ፀጥታ ሃላፊና ሻምበል መስፍን የተባሉ የቀራንዮ ክፍለ ከተማ ሽሞኞች መሆናቸው የገለፀው መረጃው ህዝቡ  የተነጠቀው ገንዘብ እንዲመለስለት ለሚመለከታቸው የክፍለ ከተማው አስተዳዳሪዎች ብሶቱ ቢያቀርብም ውጤት ማስገኘት እንዳልቻለና ምሬቱን እያሰማ መሆኑን መረጃው አስታውቀዋል።