Friday, April 18, 2014

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ ወረዳ የሚገኙ አስተዳዳሪዎች በግል ጥቅም ምክንያት በመካከላቸው ግጭት እንደተፈጠረ ምንጮቻችን አስታወቁ።



በመረጃው መሰረት የቡሬ ወረዳ አስተዳዳሪዎች በግል ጥቅም የተነሳ በመካከላቸው ከፍተኛ ግጭት የተፈጠረ ሲሆን መነሻውም አዳዲስ ሰራተኞች በሚቀጠሩበት ጊዜ ጉቦ እየተቀበሉ ቤተሰቦቻቸውን ወደ ስራ ለማስገባት በሚያደርጉት እሽቅድድም እርስ በርሳቸው ስለተዋወቁና መስማማት ባለመቻላቸው መሆኑን ለማወቅ ተችለዋል።
    ሌላው ወደ ግጭት እንዲገቡ ምክንያት የሆነው ደግሞ የብ.አ ዴ.ን አባል በሆኑትና አባል ባልሆኑት ሰራተኞች መካከል ባለው አለመስማማት መሆኑን የጠቀሰው መረጃው በዋናነት በወረዳው የሚገኘው የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ውስጥ ውጥረቱ በመንገሱ አባል ያልሆኑ ምሁራን መባረራቸውን ተከትሎ ህጋዊ አሰራር አይደለም በሚሉ ተማሪዎች ተቃውሞ እንዳይቀሰቀስ ከፍተኛ ስጋት እንደተጋረጠም መረጃው አክሎ አስረድተዋል።