Saturday, April 5, 2014

ዳንሻ በተባለው አካባቢ የሚኖሩ የቀድሞ ታጋዮች ወደ ስልጣን ያበቃነው የኢሀዴግ መንግስት እንቅስቃሴው ሁሉ ፀረ ህዝብ አሰራር የተጠናወቶው ነው ሲሉ በተካሄደው ህዝባዊ ስብሰባ ላይ መግለፃቸውን ምንጮቻችን ከቦታው ገለፁ።



    በመረጃው መሰረት እስከ ቅርብ ግዜ በሃገር መከላከያ ሰራዊት የበላይ መኮንኖች ውስጥ ሆኖው ሲሰሩ የቆዩ የቀድሞ የህወሃት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ታጋዮች ከሰራዊቱ ተሰናብተው ወደ ዳንሻ እንዲሄዱ ሲደረግ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮቻቸው እንደሚሟላላቸው ቃል የተገባላቸው ቢሆንም ከተሰናበቱ በኋላ ግን ከተሰጣቸው 10 ሄክታር የእርሻ መሬት ውጭ ትኩረት የሚሰጣቸው አካል ባለማግኘታቸው ምክንያት “ ኢህአዴግ አስመሳይና ከሃዲ ስርአት ነው ” ሲሉ የካቲት 5/2006 ዓ/ም ስርአቱ ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ በምሬት እንደተናገሩ የደረሰን መረጃ አስታወቀ።
    ይህ በእንዲህ እንዳለ ኮለኔል ደመቀና ሻለቃ አሸብር የተባሉ የቀድሞ ታጋይ መኮንኖች በስብሰባው ውስጥ እንደተናገሩት የኢህአዴግ መንግስት ፍፁም ተአማኒነት የሌለው መንግስት ነው ብሎው በተናገሩበት ሰአት በወቅቱ የነበረው ህዝብ ለተናገሩት ቃል በመደገፋ ምክንያት የተበሳጩ በመድረኩን ሲመሩ የነበሩ አስተዳዳሪዎች መንግስት ከመደገፍ ይልቅ ህዝቡን ታነሳሳላችሁ በማለት በፊት ተስጥቶዋቸው የነበረውን 10 ሄክታር የእርሻ መሬት እንዲነጠቁ እንዳደረጉ መረጃው አክሎ አስረድተዋል።