Tuesday, April 1, 2014

በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን ውስጥ የሚገኙ በሙስና የተጨማለቁ አስተዳዳሪዎች ህዝቡን ለማደናገር ያዘጋጁት የማታለያ የወረቄት ሽልማት ሽረ ከተማ ውስጥ ለመስጠት በሞኮሩበት ግዜ ከህዝቡ ሂስ እደተሰነዘረባቸው ተገለፀ።



በመረጃው መሰረት የተለያዩ የማሸባረቂያ ስእላ ስእሎች በውስጡ የያዘውን የወርቄት ሽልማት ለመስጠት ከተገኙ ባለስልጣናት መሃከል የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ጎይቶኦም ይብራህ በወቅቱ ለተገኘው ህዝብ ይቅርታ አድርጉልን የሚል የተለሳለሰ አስመሳይ ንግግር ካሰማ በኋላ በጉቦና መጠኑ ባለፈ የግብር አከፋፈል ፍዳውን ያየ የሽረ እንዳስላሴ ከተማ ነዋሪ በዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ እልፍየስ ታደሰና የዞኑ ፀጥታ ሃላፊ አቶ ደስታ የተዘጋጀውን ሽልማት አያስፈልገንም ብሎ እንደተቃወመው ለማወቅ ተችለዋል።
     ይህ በየካቲት 26/2006 ዓ/ም በተካሄደው ስብሰባ ላይ በዞኑ አስተዳደር የቀረበው በፖስተር የተዘጋጀው ሽልማት ያካባቢው ህዝብ ድርጅታችን ተዘግቶ ከባድ ኪሳራ ላይ ከውደቅን በኋላ ሽልማቱ ምን ይጠቅመናል አንቀበልም ብለው ከተቃወሙት መካከል አቶ ተስፋይ የተባሉ  ባለፋርማሲና እቶ ግደይ የተባለ ባለሆቴል የሚገኙባቸው በርከት ያሉ ወገኖች እንደተቃወሙት መረጃው አስታውቀዋል።