በደረሰን ዘገባ መሰረት በባህርዳር ከተማ በሚገኘው የአውቶብስ መናሃሪያ በር ላይ ጉንበት 11,2005 ዓ/ም
አቶ በሪሁን የተባለ ዜጋ በሌሊት ታርዶ ሞቶ መገኘቱንና ገዳዮችም እንዳልተያዙ ቷውቃል፣
ወንጀሉ የተፈጸመው አንድ የፌደራል ፖሊስ አባል ጉንበት 4,2005 ዓ/ም ከምሽቱ 3፣00 ሰኣት በየሞነሪያ
ቤቱና በየጎዳናው እየዞረ ለአንድ ሰዓት ያህል የእሩምታ ተኩስ ባገኘው ሰው ላይ በመተኮስ አንድ ህጻንና አራት ሴቶች የሚገኙበት
14 ሰዎችን በጭካኔ ገድሎ ሁለት ሰዎችን በማቁሰል እራሱን ካጠፋ ብሁዋላ መሆኑን ነው፣፣
በተመሳሳይ በሰሜን ጎንደር ዞን ፤ በታች አርማጭሆ ወረዳ አብርሃ ጅራ በተባለ አከባቢ ጉንበት
5,2005 ዓ/ም 8 ሰዎች በጩቤ ተወግተው ፥ አራቱ ወዲያውኑ ሲሞቱ ቀሪዎቹ በከባድ ቆስለው በጎንደር ከተማ በሚገኘው ሆስፒታል
የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፣፣
በአሁኑ ግዜ በአማራ ክልል እየታየ ያለ የጸጥታ መደፍረስ ኗሪውን ህዝብ እጅግ እያሳሰበው መምጣቱንና በየቦታው
ለተፈጸሙት አሳዛኝ ድርጊቶችም አንድም ወንጀለኛም ቢሆን ተይዞ እስካሁን ድረስ ወደ ህግ ስላልቀረበ ሁኔታው የህዝቡን ስጋት አባብሶታል፣፣