Sunday, July 27, 2014

የአማራ ክልልና የትግራይ ክልል አርሶ አደሮች ፍትሃዊነት በጎደለው የወያኔ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ የግብርና የመሬት አስተዳደር ምክንያት ሃምሌ 19 /2006 ዓ/ም እንደተጋጩ ምንጮቻችን ከስፍራው አስረድተዋል፣፣



በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ልዩ ስሙ ግጨው በተባለ ቦታ በትግራይና በአማራ ክልል አርሶ አደሮች መካከል የተፈጠረው ከባድ ጥላቻ መነሻው ስርዓቱ  በሚከተልው ከፋፍለ ግዛ የሚለው ፖልሲ  የሁለቱ ክልል ነዋሪዎች በይገባኛል የሚል የተነሳ  ግጭት እንደሆነ ከአካባቢው የደረሰን መረጃ አስረድቷል፣፣
   በስርዓቱ ባለስልጣናት ስምምነት በሁለቱ የክልሉ ነዋሪዎች መካከል አጋጥሞ ያለው ጥላቻ ወደ ከፋ ደረጃ ስለደረሰ ሁኔታውን እንዲያረጋጉ ተብለው ከሁለቱ ክልሎች የተላኩ የስርዓቱ  ልዩ ሃይሎች ተረዳድተው መስራት ባለመቻላቸው እርስ በራሳቸው በጥይት ተታኩሰው ከአማራ  ክልል 3 ሞተው 5 ቱ ሲቆስሉ ከትግራይ ክልል ደግሞ አንድ ክንፈ ሃጎስ የተባለው ሲሞት አግደው ታምሩ የተባለው ደግሞ እንደቆሰለ መረጃው ጨምሮ  አስረድቷል።
   ጸረ ህዝብ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስርዓት በምሸርቦ  ተንኮል  እስከ መገዳደልና የአካል መጉደል የደረሰ ጥላቻ ሲያጋጥም የቆየ ሲሆን አሁንም በከፋ መልኩ እየቀጠለ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፣፣