Sunday, July 27, 2014

የሽራሮ ከተማ አስተዳደር ለቤት አከራዮችና ተከራዮች ከመጠን በላይ የሆነ ግብር እንዲከፍሉ እያስገደዳቸው መሆኑን ምንጮቻችን ከስፍራው ገልፀዋል፣፣



በደረሰን መረጃ መሰረት በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን በሽራሮ ከተማ ቤት ሰርተው የሚያከራዩም ሆኑ የሚከራዩ ዜጎች በከተማዋ አስተዳዳሪ አከራይተው ከሚያገኙት ገቢ ያልተመጣጠነ ግብር ሲከፍሉ ተከራዮችም ከመጠን በላይ ግብር እንዲከፍሉ እየተገደዱ በመሆናቸው ምክንያት ምሬታቸውን እያሰሙ መሆኑ ታውቋል፣፣
     የሽራሮ ከተማ አስተድደር እየተከተለው ያለው የግብር አሰባሰብ ፍትሃዊነት የሌለውና የተዛባ አሰራር ሲሆን በጥናት ባልተደገፈ የግብር አሰባሰብ ምክንያት ነጋዴዎች፤ አከራዮችና  ተከራዮች ለከፍተኛ ችግር እያጋለጣቸው መሆኑን ምንጮቻችን አስረድተዋል፣፣
     በመጨረሻም ከቤት አከራዮችና ተከራዮች መጠኑ ያለፈ ግብር እንዲከፍሉ ከተገደዱት መካከል ውስጥ በረከት ቦኽረፅዮን 16 ሺህ ብር፥ ፀጋይ ዮውሃንስ 30 ሺህ ብር፥ እንዲሁም ተስፋሁን ገብረፃድቃን የኤሌክትሮኒክስ ባለቤት 65 ሺህ ብር፥ በአስተዳደሩ ተገደው እንደከፈሉ ለማወቅ ተችሏል፣፣