Sunday, July 27, 2014

በትግራይ ምእራባዊ ዞን ሑመራ ከተማ የሚገኙ የጉምሩክ ሃላፊዎች በኮንትሮባንድ ስም ከነጋዴዎች የተቀማ ንብረት በሌሊት እያስወጡ በመሸጥ ላይ እንዳሉ ተገለጸ፣፣



በመረጃው መሰረት በሑመራ ከተማ ውስጥ የሚገኝ አቶ ሃይለማርያም የተባለ የጉምሩክ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ቴሌቬዥንና ላፕቶፕ የመሳሰሉትን ንብረቶች በሌሊት እያስወጣ ሲሸጥ እንደቆየና አሁንም ይህን የሌብነት ስራው እየቀጠለበት መሆኑን ሃምሌ 07/2006 ዓ/ም በፅህፈት ቤቱ በተደረገው የሰራተኞች ስብሰባ እንደተጋለጠ ሊታወቅ ተችሏል፣፣
    ለዚህ አስነዋሪ የስርቆት ስራ እየተቃወሙት ካሉት የፅህፈት ቤቱ ሰራተኞች መካከልም አቶ አፈወርቂ አታላይ የተባሉ የፅህፈት ቤቱ አባል ለምን የህዝብ ንብረት እንደፈለጋችሁ ትሸጡታላችሁ እያለ እያተቃወማቸው በመሆኑ በዚህ ምክንያት ደግሞ በፅህፈት ቤቱ ውስጥ ያለመስማማት ስፍኖ እንዳለ መረጃው አክሎ አስረድቷል፣፣