Sunday, July 27, 2014

በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን አዲ-ነብርኢድ አካባቢ የሚገኙ በመከላከያ ውስጥ በሹፌርነት የተሰማሩ ወታደሮች የጫኑት ነዳጅ በመሸጥ ለግል ጥቅማቸው እያዋሉት እንዳሉ ምንጮቻችን አስታወቁ፣፣



እነዚህ በአዲ-ነብርኢድ የሚገኙ የወያኔ ኢህአደግ ወታደሮች ለሰራዊቱ አገልግሎት በመስጠት ላይ ላሉ ተሽከርካሪዎች እንዲሆን ተብሎ የተላከ ነዳጅ  በስራ ላይ ሳይውሉ በመሸጥ ለግል ጥቕማቸው እየተጠቀሙበት እንዳሉ የገለፀው መረጃው በዚህ ስራ ተሰማርተው ካሉት መካከልም የታርጋ ቁጥር 02066 የሆነች ወታደራዊ መኪና የያዘ ሹፌር ጭናው ለነበረው ነዳጅ ለሲቪል ነጋዴዎች በመሸጥ ለግል ጥቕሙ እንዳዋለው ታወቀ፣፣
ይህ የኢህአደግ መከላከያ ሰራዊት አባል የሆነው ሹፌር መኪናዋ ጭናው የነበረችው ነዳጅ ሃምሌ 12/ 2006 ዓ/ም ከአዲ-ነብርኢድ ወደ ማይ-ዓሶ የተባለ አካባቢ ሊያደርሰው የተሰጠው ነዳጅ ወደ ቦታው ሳይደርስ ለአንድ ጀሪካን ነዳጅ በ350 ብር ሂሳብ ለሲቪሎች እንደሸጠው የገለፀው መረጃው ይህ የሙስና አሰራር የሰራዊቱ የበላይ አዛዦች እጅ ይኖረዋል የሚል እምነት እንዳለ የተገኘው መረጃ ጨምሮ አስረድቷል፣፣