በመረጃው መሰረት ከ2005
ዓ.ም ጀምሮ የስርዓቱ ካድሬዎች በእንደርታ ወረዳ የእግሪ-ሓሬባ ቀበሌ
ነዋሪዎች ለሆኑት በግዴታ ወደ መቐለ ከተማ አስተዳደር እንዲጠረነፉ
ሲያደርጉት የነበረው ሓይል የተሞላው እኩይ ተግባር በእግሪ-ሓሬባ ነዋሪዎች ተቃውሞ ስላጋጠመው ለህብረተሰቡ ከህክምና ከትምህርትና
ከሌሎችም ማህበራዊ አግልግሎቶች ተጠቃሚ እንዳይሆን ከልክለውት እንደሚገኙ ታውቋል፣፣
በተጨማሪም ወደ መቐለ ከተማ አስተዳደር መሆን አንፈልግም በማለታቸው
ብቻ ከታሰሩት ንፁሃን ዜጎቻችን መካከል ወ/ሮ አልጋነሽ ገብሩ፤ አቶ ሙዑዝ በላይ፤ አቶ ሓለፎም ገብረሚካኤል፤ አቶ አያሌው በለጠና
አቶ ከለል የተባሉ የሚገኙባቸ በርከት ያሉ ዜጎቻችን እንደሆኑ በመጥቀስ
ለዚህ አስነዋሪና ግፍ የተሞላበት ተግባር እየፈፀሙ ያሉ የስርዓቱ ቀንደኛ ካድሬዎች ደግሞ መምህር ሃፍቱ አሰፋና መምህር መረሳ ወይንም
ኤሊያስ በሚል ስም የሚጠራው መሆናቸውን መረጃው አክሎ አስረድተዋል፣፣