Friday, July 18, 2014

በትግራይ ማእከላዊ ዞን፤ ጧንቋ አበርገለ ወረዳ፤ የጭላ ቀበሌ አሰተዳዳሪዎች ማዳበርያ በመሸጥ ላይ ወገናዊነትና ልዩነት እየፈፀሙ መሆናቸውን ምንጮቻችን ከቦታው ገለፁ፣፣



አስተዳዳሪዎቹ ስልጣናቸውን ተጠቅመው የህወሃት ኢህአዴግ አባላት ለሆኑትና ወዲያውኑ ክፍያ ለሚፈፅሙ ሃብታሞች እንደፈለጉት ሲሰጥዋቸው ከዋጋው በላይ በሆነ ክፍያ ለተወሰኑት  አርሶ አደር ገበሬዎች እንዲሰጡ ከተደረገ በኋላ አብዛኛዎቹ ሳይወስዱ ተጭርሰዋል እንደተባሉ  የደረሰን መረጃ አስታወቀ፣፣
     ይህ በሰኔ 17/2006 ዓ/ም በቀበሌዋ የተካሄደው የመዳበርያ የመሸጥና የማከፋፈል ስራ አብዛኛው ገበሬ ማዳበርያ ሳይገዛ እንደቀረና ከዚህ በፊት የወያኔ ባለስልጣኖች ለሁሉም የሚበቃ ማዳበርያ ተዘጋጅተዋል እያሉ ቆይተው ተግባር ላይ ግን ሳይፈፀም በመቅረቱ ምክንያት ገበሬዎቹ መፍትሄ እንዲደረግላቸው ላቀረቡት አቤቱታ ሰሚ አካል እንዳላገኙ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል፣፣