Thursday, July 24, 2014

በቃፍታ ሁመራ ወረዳ ውስጥ የሚገኙ የፖሊስ አዛዦች ህጋዊ ባልሆነ ስራ ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ የተገኘው መረጃ አስታወቀ።




     ታማኝ ምንጮቻችን ከወረዳው እንደገለፁት በቃፍታ ሁመራ ወረዳ ውስጥ በምክትል አዛዥነት እየሰራ የሚገኘው ኮማንደር ዝናቡ የተባለው ፖሊስ እያገለገልኩት ነኝ ከሚለው ህዝብ ከፍተኛ ግቦ በመቀበልና ሰዎች ወደ ሱዳን በማሸጋገር ስራ ላይ እንደተጠመደ ታውቋል።
     ኮማንደር ዝናቡ ቀደም ብሎ ተመሳሳይ በሆነ ወንጀል በቀጥጥር ስር ከዋለው ኮማንደር ይርጋለም ከተባለው የፖሊስ አዛዥ ጋር ትስስር እንዳለው የገለጸው ህዝቡ ተይዞ መጠየቅ አለበት በመለትም ብሶቱን እያቀረበ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
    በተመሳሳይ መንገድ በፅህፈት ቤቱ የሚሰራው መርማሪ ፖሊስ ሳጅን ዓወት መንገሻ የተባለው በግቦና በዘመድ አዝማድ ፍትህን በገንዘብ እየለወጠው መሆኑን ከስራው ቅርበት ያላቸው አካላት ቢያውቁትም እስካሁን ድረስ ግን የተወሰደበት እርምጃ ባለመኖሩ ምክንያት አሁንም ችግሩ እየቀጠለ መሆኑን መረጃው አክሎ አስረድቷል።