Thursday, July 24, 2014

በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን ዓዲ ዳዕሮ ወረዳ፤ ዕጉብ ቀበሌ ውስጥ የሚገኘው ህብረተሰብ በውሃ እጥረትና ሌሎች የመሰረተ ልማት እጥረት ምክንያት ለተለያዩ ችግሮች መጋለጡ ምንጮቻችን ከቦታው ገለፁ።



በመረጃው መሰረት የዓዲ ዳዕሮ ወረዳ ዕጉብ ቀበሌ ዓዲ ርእሶ፤ ታብር፤ ዓዲ እከለና ጤረር የሚገኙ ነዋሪዎች በአካባቢያቸው ህክምና፤ ትምህርት ቤት፤ ጥርጊያ መንገድ፤ ሌሎች መሰረተ ልማቶችና እንዲሁም እንደ ዘይትና ስኳር የመሳሰሉት ከገበያ በመጥፋታቸው ምክንያት በስርአቱ ላይ ምሬታቸውን እያሰሙ እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል።
    ነዋሪዎቹ በቀበሌዋ አስተዳዳሪ እቶ ገብረዝጊአብሄር በተደረገላቸው ስብሰባ ላይ በህክምናና የጥርግያ መገድ እጥረት በርካታ ህሙማን ለስቃይና ለሞት እየተጋለጡ ናቸው ብለው እንደተናገሩ የገለፀው መረጃው ትምህርት ቤት የሚባል ባካባቢያቸው ባለመኖሩ ሳቢያም ልጆቻቸው ለድንቁርና ስለተጋለጡ መፍትሄ እንዲደረግላቸው ላቀረቡት ጥያቄም ያካባቢው አስተዳዳሪ እኔ በተደጋጋሚ ጠይቄያለህ የራሳቹህ ምርጫ ማድረግ ትችላላችሁ በማለት እንደመለሰላቸው መረጃው አክሎ እስረድቷል።