Thursday, July 24, 2014

በቅርብ ጊዜ የተደረገው የመንግስት ሰራተኞች የደመወዝ ጭማሪ የሁመራ ‘ከተማን ማህበራዊ የኑሮ ውድነት አባብሶት እንደሚገኝ ምንጮቻችን አስታወቁ።



በትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን በሰቲት ሁመራ ከተማ ለሚኖር  ህብረተሰብ በአላቂ ነገሮች የዋጋ መናር ሲቸገር እንደቆየና አሁን ተደረገ የተባለው  የመንግስት ሰራተኞች የደመወዝ ጭማሪ ጋር ተያይዞም ዋጋ መናር ብቻ ሳይሆን በከተማው እንደ ስኳር፤ ዘይት፤ ፊኖ ዱቄትና ሌሎችም ተዛማጅ ነገሮች ጠቅልለው መጥፋታቸውን የከተማውን ነዋሪ ህዝብ መሰረት በማድረግ የደረሰን በረጃ አመለከተ።
    በከተማዋ ውስጥ አከፋፋይ ድርጅቶች ተብለው በስርዓቱ አስተዳዳሪዎች ተወክለው የሚገኙ ነጋዴዎች በአስተዳድሩ የተሰጣቸውን ስኳርና ዘይት ለተጠቃሚዎች በተገቢው መንገድ ከማከፋፈል ይልቅ ጨርሰናል እያሉ በመጋዝናቸው ደብቀው በመቆየት ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ለአንድ ሊትር ዘይት እስከ 60 ብር እየሸጡ መሆናቸውን ምንጮቻችን አስታወቁ።
    በመጨረሻ መረጃው እንዳስረዳው በስልጣን ያለው ስርዓት ለመንግስት ሰራተኞች በቂ የሆነ የደመወዝ ጭማሪ አድርጌአለሁ እያለ በሚቆጣጠራቸው ሚዲያዎች እያስተላለፈ ያለውን ፕሮፖጋንዳ ተከትሎ በሁሉ ያሃገራችን ከተሞች ሳይውል ሳያድር የዋጋ ንረት እንዳሳየ በመግለፅ በመዲናችን አዲስ አበባም ነዋሪዎቹ የሚቆርሱት ዳቦ አጥተው በችግር ላይ እንደሚገኙና ሁኔታውም በሁሉም ያሃገራችን አካባቢዎች በመስፋፋቱ ምክንያት ዜጎቻችን አደጋ ላይ ወድቀው ምሬታቸውን በመግለፅ ላይ እንዳሉ መረጃው አክሎ  አስረድቷል።