Thursday, July 17, 2014

የወያኔ ኢህአዴግ ስርአት በሰላም አስከባሪ ስም እየመለመለ የሚልካቸውን የፌደራልና የመደበኛ ፖሊስ ሰራዊት ቀጣይ አመት በሚደረገው ምርጫ ላይ ህዝባዊ ተቓውሞ ቢነሳ የስርአቱ ወገን ሆነው ህዝቡን እንዲጨፈልቁለት በማሰብ እንደሆነ ተገለጸ፣፣



የገዢ ስርአቱ  መሪዎች ስልጣን ላይ ለመቆየት ካላቸው ፍላጎት የተነሳ 2007 ዓ/ም በሚካሄደው የይስሙላ ምርጫ ላይ አደናግረው አሸነፍን ማለታቸው እንደማይቀር ከወዲሁ ስለሚያውቁት ዜጎች የህዝብ መብት ይከበር ብለው በሚቃወሙበት ሰአት ከወዲሁ በጥቅም ተደልለው ህዝቡን የሚጨፈጭፉ ሃይሎች ለማዘጋጀት በማሰብ ቀደም ብለው በሰላም አስከባሪነት ተልከው ለነበሩት የሰራዊት አባላት በመቀነስ በምትኩ የፌደራልና የመደበኛ ፖሊሶችን መልምሎ እየላካቸው መሆኑን የደረሰን መረጃ አስታወቀ፣፣
     እነዚህ ከህዝቡ ተነጥለው የሚገኙና በቀጣይ ስልጣናቸውን ለማቆየት ሲሉ ላይና ታች እያሉ የሚገኙ የስርአቱ ባለስልጣኖች እምነታቸው በመከላከያ ሰራዊት፤ ደህንነት፤ ፌደራልና መደበኛ ፖሊስ ላይ አድረገው እየጠበቁ መሆናቸውና እነሱ የሚፈልጉትን ትእዛዝ እንዲያስፈፅሙላቸው እንደመሳርያነት ሊጠቀሙበት በማሰብ። በሰራዊቱ ውስጥ የሰላም አስከባሪ ምልመላ በማካሄድና በጥቅም የተሳሰረ ሰይጣናዊ ውድድር እንዲኖር በማድረግ ቀጣይ ህዝቡን ጨፍለቀው ለማምበርከክ የታሰበ እንደሆነ መረጃው አክሎ አስረድቷል።