Thursday, July 17, 2014

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ለሚኖሩ የጎዳና ተዳዳሪዎች በስርአቱ ካድሬዎች ስራ ሊሰጣችሁ ነው በሚል ምክንያት እያተታለሉ ወደ አፋር ክልል እየወሰድዋቸው እንደሆነ ታወቀ፣፣



 እነዚህ በስራ አጥነትና ሌላ ምክንያት በአዲስ አበባ ከተማ ለጎደና ተዳዳሪነት ተጋልጠው የቆዩ በሺዎች የሚገመቱ ወገኖች በስርአቱ ላይ አመፅ እንዳያስነሱ ስጋት ላይ የወደቁት የስርአቱ ባለስልጣኖች ልዩ የሞያና ቴክኒክ ስልጠና አስተምረን የስራ እድል እንከፍትላችሁአለን ብለው በማታለል ወደ አፋር ክልል እያጓጓዟቸው መሆናቸውን የተገኘው መረጃ አስታወቀ፣፣
    መረጃው በማስከተል ወደ አፋር ክልል የተወሰዱትን የጎዳና ተዳዳሪዎች በክልሉ እየተሰራ ባለው የክንደሆ ግድብ ውስጥ በመስኖ ስራ ላይ በማሰማራት ጉልበታቸውን በዝቅተኛ ክፍያ እየበዘበዝዋቸው መሆኑን የገለፀው መረጃው ለወጣቶቹ በገንዘብ በመደለል በብዙሃን መገናኛ ቀርበው ስርአቱን የሚያመጉስ ሃሳብ እንዲሰጡና ቀጣይ ለሚካሄደው የ2007 የይስሙላ ምርጫ ላይ ህዝቡ ለወያኔ ኢህአዴግ ስርዓት እንዲመርጥ ቅስቀሳ እንዲያድረጉ እያስገደድዋቸው መሆኑን ለማወቅ ተችለዋል፣፣
    ይህ በእንዲህ እንዳለ ስልጣን ላይ ያለው ስርአት ሚድያ ላይ እንዲቀርቡ በማድረግና ከተሰጣቸው ሃሳብ ሳይወጡ እንዲናገሩ ቢያደርግም የአዲስ አበባና ሌላው የአካባቢው ህዝብ ግን 2007 ዓ/ም ሊካሄድ ታስቦ ያለውን የይስሙላ ምርጫ ተከትሎ ሊከሰት በሚችለው የህዝብ ተቃውሞ ላይ ዋነኛ ተዋንያን እንዳይሆኑ በመስጋት እንጂ ሌላ ምክንያት እንደሌለው ህዝቡ በተለያየ መንገድ ሁኔታውን እያጋለጠው መሆኑን የደረሰን መረጃ አክሎ አስረድቷል፣፣